አዚህ ሀገር ካልተማረዉ የተማረው በሞራል ባርነት በአስተሳሰብ ድህነት ዉስጥ ነው!!!

ኢትዮጲያ ያደረገችው የነፃነት ትግልም ሆነ አፍሪካዊያን ያደረጉት የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል በዋናነት #በፖለቲካዊ ጉዳች ላይ ያተኮረ ስለነበር, በማሕበራዊ እሴቶቻችን እና በኢኮኖሚያዊ ጥቅሞቻችን ከማስጠበቅ አንፃር እኛ አፍሪካዊያን አሁንም በቅኝ አገዛዝ ቀበር ሥር ነን::

የነፃነት ትግሉ በዋናነት በፖለቲካዊ ነፃነት ላይ የተመሠረተ ስለ ነበር በማሕብረሰባዊ ዕሴቶቻችን ላይ የደረሰውን ኪሣራ ትኩረት ሣይሰጠዉ አልፏል:: በነገሮች ላይ ያለን አመለካከት ሆነ የግል አስተሣሠባችን ሣይቀር በዚህ ተፅዕኖ ስር ነው:: ለምሣሌ
“በተማረ” ና “ባልተማረ” ኢትዮጲያዊ መካከል ያለ መሠረታዊ ልዪነት ምንድን ነው?
እንደ እኔ ሁለት ናቸው::
1) ያልተማረዉ ሰዉ አስተሣሠብ እና አመለካከት በነባር የማሕብረተሠብ ዕሴቶች ላይ መሠረት ያደረገ ነው:: የተማረዉ ግን ት/ት ቤት (ኮሌጅ) ሲማረው ያልገባውና ከአሜሪካና ህንድ ፊልሞች ውስጥ በቀሰመው ዕሴት እና አዉቀት የአስተሣሠብ እና የአመለካከት አድማሱን አስፍቷል!i

2) ያልተማረ ኢትዪጲያዊ እዉቀት በነባራዊ ሁኔታ ላይ መሠረት ያደረገ ሲሆን የተማረው ሰው እውቀት ግን አውሮፓና አሜሪካ ባለ ነባራዊ ሁኔታ ላይ መሠረት ያደረገ ነው:: በት/ት ቆይታው የእንግሊዘኛ ቃላትን እንደ ዳዊት ሲደግም የከረመ አዕምሮ, የቨመደደዉን ከነባራዊ እውነታ ጋር ማመሣጠር ቢሣነው
“ቲዎሪ-ሌላ-ተግባር-ሌላ”
የሳይንስን መሠረታዊ እሣቤ-“የእዉቀት እና የእዉነታ አንድነትን” በመጣስ; እዉቀቱን “ኢ-ሳይንሳዊ” በማድረግ ከሃላፊነት እራሱ ነፃ አወጣ::

እዉነታን አንሸዋሮ የሚያሣይ ‘እዉቅት’ የእራሱን ችግር ከማየት የታወረ ነው:: ይሄ ሸዉራራ እዉቀት የተንሸዋረረዉ በራሱ ሣይሆን በተደነባበረ የት/ት ሥረዓት ነው:: Our Educational system is based on wrong Epistemological assumptions! ቅኝ ገዢዎች ሌሎች የአፍሪካ አገራት ላይ ሲጭኑባቸዉ “#ኢትዪጲያ” ከአዉሮፓ አምጥታ እራሷ ላይ ጫነች:: የተማረውም ገበሬ “በእንግሊዘኛ ካልተማረ ምን አወቀ ብሎ ተመፃደቀ::”

Advertisements