እኔ ምለው?…አሁን እንደው ማን-ይሙት ኢትዮጲያ ውስጥ የፖለቲካ ሙህራን (Political Elites) አሉ? ….ወፍ የለም!

ዴሞክራሲ በሁለት የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል የሚደረግ ትግል ውጤት ነው:: ጥንታዊው የግሪክ ዴሞክራሲም ሆነ ዘመናዊው የምዕራብዊያን ዴሞክራሲ በሙህራን (Educated Elites) እና ሥልጣን ላይ ባሉት (Ruling Elites) መካከል በተደረገው ትግል የመጀመሪያዎቹ አሸንፈው ሥልጣን መጋራት ወይም መገደብ በመቻላቸው ምክኒያት ነው የተገነቡት::

ሥልጣን የያዙት (የተጋሩት) ደግሞ “ባለሥልጣን” ሲሆኑ ከቀሩት ሙህራን ጋር ይፋጠጣሉ:: እራሱንና የተቀረዉን የማሕብረሰብ ክፍል በተሻለ ሁኔታ አደራጅቶ መምራት የቻለው እያሸነፈ የለውጥ ሂደቱ ይቀጥላል::

በኢትዮጲያም ተመሣሣይ የለውጥ ሂደት ነው ያለው:: ሙህሩ ዐፄ-ሃይለሥላሴን “ከፀሐዩ ንጉስነት” ወደ መሬት አዉርዶ ባለሥልጣን ለመሆን ሲቃረቡ “ባለጠመንጃ” በአቇሯጭ ቦታውን ያዘው:: “what is a soldier?”-ቢሉ-“whatever his superior wants him to be” አንዲሉ: ባለ-ጠመንጃው ሀገሪቱን በሚያውቀው ልክ መምራት ሲጀምር ሙህራኑ ባለጠመንጃን በጠመንጃ ለማስወገድ ተነሱ::

ባለጠመንጃን መሃል-አራዳ የተፋለሙት ሙህራን በጠመንጃ አለቁ:: ከእልቂቱ የተረፉት በጣም ጥቂት ሙህራንም “ባለጠመንጃን ጥግ ይዞ ነው” ብለው በግዜ ደደቢት ጫካ ገብተው የነበሩት ሲሆኑ ይኼው ዛሬ “ባለሥልጣን” ሆነዋል::

“….ባለሥልጣን የሆኑት ሙህራን #ከቀሩት #ሙህራን ጋር እየታገሉ #ዴሞክራሲያዊ #የለውጥ #ሂደቱ ይቀጥላል” ብዬ ነበር:: አዎ…. የኼ ሂደት በዛሬይቱ ኢትዮጲያ የለም:: ለምን ቢባል “ባለጠመንጃው” ሙህር የሚባልን በሙሉ ከነ-ሥሩ ነቅሎ አጥፍቶት የቀረው “አራሙቻ” ብቻ ስለሆነ:: ጫካ ሣይገቡ የተረፉት ለባለጠመንጃው አቤት-ወዴት ሲሉ የነበሩ አሽቃባጮች ወይም አስሮ-ገርፎ “ፖለቲካ” የሚለዉን ቃል “ፖለቲካ እሳት ነው” ከሚለዉ ዐረፍተነገር ወጪ ፈፅሞ እንዳይጠቀሙት አስምሎ የለቀቃቸው ናቸው::

“ፖለቲካ እሳት ነው” እና “ዝም ያሉ ናቸው የተረፉት” የሚሉት ዐ.ነገሮች እየለፈፉ እንዲኖሩ ባለጠመንጃው አስምሎ ነው የለቀቃቸው:: ይኼን እየሰማ ያደገ ትውልድ ደግሞ በ”ዘሬ” እና በ”ሃይማኖቴ” እስካልመጣ ድረስ ፖለቲካ የ”ወሬኞኝ” እና “ሁሉን-ነገር መቃዎም የሚወዱ” ሰዎች ተግባር እነደሆነ አድርጎ ፖለቲካን ከአዕምሮው አውጥቶታል (Compartmentalized Minds)::
በመሆኑም ሙህራን ሲጠፉ እነ አስራት ጣሴ: እነ አየለ ጫሚሶ … እና መሠሎቻቸው “ፖለቲከኛ” ሆኑ::

ይኼ ትውልድ የራሱን አዲስ የፓለቲካ ሙህራን (Political elites) እስካልፈጠረ ድረስ በአራሙቻ ፖለቲከኞች የሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ የለውጥ ሂደት አሁን ተሰንቅሮ ከቆመበት ንቅንቅ አይልም::

https://ethiothinkthank.wordpress.com