ኢህአዴግን የምታሸንፉት በሜዳው ነው::

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለ-ኢህአዴግ ሊቀበሏቸው የሚገቡ መሠረታዊ እውነታዎች:-

1) በተለይ ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ሃገሪቱን ከሞላ-ጎደል በተጠና መንገድ እየመራት ነው:: የሚሄድበትን መንገድ (ቢያንስ አቅጣጫውን) ያውቃል::

2) ኢህአዴግ የሚከተለው “ፖለቲካል ኢኮኖሚ” የሃገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ እና የአለም-አቀፉን የሃይል ሚዛን ከግምት ያስገባ ነው:: የNeo-Liberalism ቁንጮዎች IMFና World Bank ለአመታት ብለው-ብለው ሲያቅታቸው (ሲሰለቻቸው) ትክክለኝነቱን ከሞላ-ጎደል ተቀብለውታል::

3) አሁን ያለው የፌዴራሊዝም አወቃቀር ወደ የትኛዉም መዎቅር እንዳይቀየር: ከቤሄር-በሄረሰቦችና ህዝቦች “የማንነትና እኩልነት” ጥያቄ ጋር ተጣምሮ ስር ሰዷል:: ይህን ስለመቀየር የሚያትት የፖለቲካ አጀንዳ ያለው ፓርቲ የብዙሃንን ድጋፍ ለማግኘት አይችልም::

4) የኢህአዴግ እና የተቃዋሚዎች ደጋፊዎች ስብጥር:
ኢህአዴግ.. የሃይል አሠላለፍ ሚዛኑ በዋናነት በብዙሃኑ (ገበሬ) ላይ መሠረት ያደረገ በመሆኑ ዘላቂ የሆነ ድጋፍ እንዲያገኝ ያስችለዋል:: ኢትዮጲያ የ”ከተማ-ዐፈ-ጮሌ” ሳይሆን የ”ባለ-አገሩ” ነች:: መሠረታዊ ችግሮቹን ካቃለልክለት የማይነጥፍ የፖለቲካ ድጋፍ ይሰጥሃል::
የተቃዋሚዎች
– በኢህአዴግ ካድሬ የተበደለ ወይም ከኢህአዴግ አኩርፎ የወጣ:
– ህውሐት/ኢህአዴግን “ጠባብ ቤሔርተኛ” ሲሉ የኖሩና የእነሱ የሕይወት ዘመን ትግላቸው ስኬት በድርጅቱ ውድቀት (የሃገሪቱም ቢሆን) ላይ የተመሠረተ “የፖለቲካ ሃሎች”

በአጠቃላይ: ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦችን ከግምት ሳያስገባ የሚነቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲ የ”ቢሆን-አለም ሰዎች” መሰባሰቢያ ከመሆን ባለፈ የብዙሃንን ድጋፍ ማግኘት አይችልም::

መፍትሄው:-
የኢህአዴግን ድርጅታዊ አወቃቀርን እንደ-መነሻ በመውሰድ መደራጀት-በዚህሞ የፖለቲካ “ጨዋታውን” በኢህአዴግ “ሜዳ” ማድረግ:: እቤቱ መግባት!! ያኔ.. ኢህአዴግ በመዋቅራዊ ሥራዎቹ መመፃደቁ ይቀርና በጭፍን ታማኝነት ተጀቡኖ “በቀረጥ ሰብሳቢነት” የጨቀየ ገመናውን መሠወር ይሣነዋል!!!