ከጥሩና_ከመጥፎ_ባሻገር በሽመልስ_ሰዩም

በሆነ ግዜና ቦታ የሆነ ነው:: ቻርለስ ዳርዊን; ሲግመንድ ፍሮይድ; ፌሬድሪክ ኒቼ; እና ካርል ማርክስ ሆነው ቀደዳቸውን ይቀዳሉ:: …..

ዳርዊን “…..Origin of Species በተባለው መፅሐፌ ስለ ዝግመተ-ለውጥና ሰለ የሰው ልጅ አመጣጥ ብዙ ብያለሁ:: እንዳልኩት ማንኛውም ነገር እንዳልተፈጠረ እና የፈጣሪን መኖር የሚያመለክት ምንም መረጃ እንደሌለ ግልፅ ነው:….”

ኒቼ “…..ይሄ ዝግመተ-ለውጥ የምትለው ነገር እራሱ ሀሣቡ ‘ዘገምተኛ’ ነው!…..ስለ እግዚያብሄር መኖር እና አለመኖር ማረጋገጫ አይሆንም:: ምክኒያቱም እግዚያብሄር ኖሮ ነገሮቹን ‘በዝግመታዊ ለውጥ ይሁኑ’ ብሎ ፈቅዶ ቢሆን የአንተ ቲዎሪ አፈር-ጋጠ ማለት ነው…. እራሱ ‘ዝግመታዊ ለውጥ ቲዎሪ’ ሳይንስ ሣይሆን ሌላ ሐይማኖት ነው የሚመስለው……………………………………………………………………………………..እንደው አሁንስ ከጥሩና ከመጥፎ ባሻገር ሌላ አማራጭ ቢኖር እንዴት ጥሩ ነበር::”