ለ”እኔ” የዴሞክራሲያዊ ያልሆነ ሕብረተሰብ ዴሞክራሲ አ.ይ.ገ.ባ.ው.ም!!!!!!!!!!

ዴሞክራሲያዊ ሥረዓት ማንኛውም ግለሰብ ያመነበት ሆኖ እንዲኖር እንጂ በሕብረተሰቡ ‘እኛን ካልመሰልክ’ ተብሎ የሚገደድበት አይደለም:: የመንግስት ሚና ግለሰቦች በሕብረተሰቡ ከሚደርስባቸው “የእኔን ምሠሉ” ጫና መጠበቅ ነው:: ይሄ ሣይሆን ቀርቶ: መንግስት የሕብረተሰቡ ወኪል ነኝ ብሎ “ያሽቃበጠ” እለት ነፃነት ብሎ ነገር አበቃላት! ያ..ን ግዜ:-
መንግስት ጨቁዋኝ ሙሰኛ;
ሕብረተሰቡ – አጉል ወግ-አጥባቂ ሃይማኖተኛ;
ግለሰቡም አላወቂ ጨለምተኛ ይሆናሉ:: ምክኒያቱም ነፃነት የጎደላት ሕይወት ውስጥ የአስተሳሰብም ሆነ እሳቤ ድርቀት እንጂ ልኽቀት ሊኖር አይችልምና!!!

የዴሞክራሲ ትግል የሚካሄደው በሕብረተሰብ እና በመንግስት መካከል ሣይሆን በሕብረተሰብ እና በግለሰብ መካከል ነው:: የዴሞክራሲያዊ መብቶች ፀር መንግስት ሣይሆን እሱን በሥልጣን እንዱቆይ የፈቀደው ሕዝብ ነው:: የነፃነት ጠላት ‘እኛን-ምሰል’ ብሎ የሚያስገድድ: ስህተቱን ስትነግረው “ከእብድት” ፈርጆት ለምትናገረው እውነት ቁብ የማይሰጥ ሕብረተሰብ ነው::