ይቺህ ‘የቤሄር ማንነት’ ጥያቄ ስትነሳ “ኢትዮጲያዊ ነኝ” የምትባለው ነገር….!!

ይቺህ ‘የቤሄር ማንነት’ ጥያቄ ስትነሳ “ኢትዮጲያዊ ነኝ” የምትባለው ነገር….!!
*******************************
በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ተንተርሰን ነገሩ እንደ ምክኒያት ከመውሰድ ይልቅ የሀገሪቱ ፖለቲካ መዋቅርዊ ለዉጥ ምክኒያት የተከሠተ እንደሆነ አድርጎ ማየት “ትምክህተኛ” እና “ጠባብ-ቤሄርተኛ” ከሚሉ ነቆራዎች ይገላግለናል::

የኢትዮጲያ (አቢሲኒያ) ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ መዋቅር በግራኝ አህመድ ከተደመሠሠ ከ300 ዓመት በሗላ እ.ኤ. 1855 ጀምሮ እስከ 1955 ያለው ግዜ ወደ ቀድሞ ቅርፁ ለመመለስ ጥረት የተደረገበት ነው::

የአማራ; ትግሬና የዬጁ-ኦሮሞች ጎንደር ላይ እርስ በእርሳቸው ተጠላልፈው የነበረ ቢሆንም የለውጥ ሂደቱ በአማራ የተጀመረና ቀጣይ ሂደቱም በዋናነት በአማራ የተመራ ነበር:: ልክ እንደ አሜሪካ ‘የአይሪሽ ነጮች’; የቻይና ‘ሀን’ ወይም ደቡብ አፍሪካ ‘ዙሉ’….በኢትዮጲያም በአብዛኛው ‘Ruling Elites’ የነበሩት አማራዎች ስለ ነበሩ; የቤሔራዊው ማንነት በዚህ ቤሄር ማንነት ጥላ ሥር እንዲወድቅ አድርጎታል:: ለምሣሌ; ‘የአይሪሽ ነጮች’ “American” ሲሉ ጥቁሮቹ “Afro-American” የቻይና ‘ሀን’ “Am Chinese” ሲል የቱርክ ዝርያ ያላቸው ቻይናዊያን ወይም ‘ቲቤቲያዊያን’ እኛጋም “Oromo First”; “Amhara First” እንላለን::

የእኛን ልዩ የሚያደርገው ጦርነቱ ሣይሆን (ከአሜሪካና አውስተራሊያ ውጪ ያለ ጦርነት የተመሠረተ ሀገር የለምና) ከ1943 ጀምሮ በ5 ዓመቱ የጣሊያን ቆይታ የተፈጠረውን ክፍተት ለመድፈንና ዘመናዊ የአስተዳደር ስረዓትን ለመዘርጋት የተሠራው ሥራ የሀገሪቱ ቤሄሮችና ቤሄረሰቦች በሁሉም ዘርፍ “አማራ” እንዲሆኑ ጫና የሚያደርግ ነበር, which is called ‘Amharanization’.

በተለይ በ5 ዓመቱ የጦርነት ወቀት አርበኛ ነበሩ በሚል በመላ የሀገሪቱ አስተዳደር መዋቅር ውስጥ ተሰግስገው የነበሩት የቀድሞ ሽፍቶች እና ወንበዴዎች በሀገሪቱ ቤሄሮችና ቤሄረሰቦች የማንነት ጥያቄ ላይ ያደረሱት ኪሣራ ይሄው እስከ አሁን እየከፈልን ነው::

የኢህአፖ’ም ሆነ ኢህአድግ መፈጥር መሠረታዊ ምኪኒያት ይሄው ታሪካዊ ስህተት ነው::

ስለዚህ ኢህአዴግ የዘረጋው አስተዳደራዊ መዋቅር ይሄ የቤሄር-ቤሄረሰቦችን የማንነት ጥያቄ በተንሸዋረረ አይኑ ያይ እና በደነቆረ ጆሮ ይሰማ የነበረን ሰዓረት ለመጨረሻ ሲያስወግደው…….እነዚህ ‘የቤሄር ማንነት’ ጥያቄ ስትነሳ “ኢትዮጲያዊ ነኝ” የሚሉት ደግሞ በተወገደው ስረዓት የታወሩና የደነቆሩ የከተማ አፈ-ጮሌዎች ናቸው::
https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements

2 thoughts on “ይቺህ ‘የቤሄር ማንነት’ ጥያቄ ስትነሳ “ኢትዮጲያዊ ነኝ” የምትባለው ነገር….!!

 1. አማርኛ መናገርህ አማራ ያደርግሃል? አማራ የሚባል ብሔር አለን? ጎጃም ውስጥ የሚኖሩት አገዉኛ የሚናገሩትም ሆነ አማርኛ የሚያወሩት ምንድናችሁ ብትላቸው ጎጃሜ እንጅ አማራ አይሉህም። ጎንደርም፣ ወሎም እንደዛው ነው። ስለዚህ እንዴት እራሳቸውን አማራ ብለው የማይጠሩትን ሰዎች አማራ ብለን እንጠራቸዋለን? ልክ የምዕራብ ፀሃፊዎች ኢትዮጵያን አቢሲንያ እያሉ እንደሚጠሩት ይሆናል።
  በርግጥ ነው እራሳቸውን አማራ እያሉ የሚጠሩ በከተማ የሚኖሩ አማርኛ ተናጋሪዎች አሉ። እነሱ ግን ያብዛኛውን ሰው ማንነት ወሳኝ መሆን አይችሉም። ብአዴን “አማራ” ብሎ የሚጠራቸው ሕዝቦችን ከህዝቡ ጋር ምንም ግንኙነት ለሌላቸው ባንዲራ(የአማራ ክልል) እና ማንነት አጋልጧል። ልክ ህውሃት የትግራይ ባንዲራ ብሎ እንደፈለሰፈው።
  አማርኛ ተናጋሪዎች ግዕዝ ይናገሩ የነበሩ አክሱማዊያን ወደ ደቡብ ሲስፋፉ የተፈጠረ ቋንቋ ነው። ከተፈጠረበት ግዜ ጀምሮ ግን የተለያዩ ቋንቋ ይናገሩ የነበሩ ህዝቦች ወደ አማርኛ ተናጋሪነት ተቀይረዋል፣ ልክ ኦሮሞዎች በሚስፋፉበት ግዜ እንደሆነው። ይህ የተለያዩ ባህሎችን መቀላቀልና ወደ አንድ ቋንቋ ተናጋሪነት መቀየር አማርኛ ቋንቋን ከብሔር ቋንቋ ወደ ሕብረብሔራዊ ቋንቋ ሲቀይረው ቋንቋውን የሚናገሩትን ሕዝቦች ደግሞ አንድ ቋንቋ የሚናገሩ የተለያዬ ባህል ያላቸው ህዝቦች አድርጓቸዋል። የኦሮምኛም ጉዳይ እንደዛው ነው።
  ስለዚህ እነዚህ ሁለት ቋንቋዎች የተነሱበትን መሠረታቸውን አልፈው ሌሎች ቋንቋዎችን በማቀፋቸው Melting pot ያደርጋቸዋል እንጂ የብሔር መገለጫዎች አይሆኑም።

  Like

 2. Yes I agree with what you said….but it does not negate the political phenomenon of 2he country immediately after the withdrawal of Facist Italy…the Amharanization, which severly damages the socio-political sphere of the nation. I think it is because of this phenomenon that:
  የኢትዮጲያ የቤሄርና የማንነት ፖለቲካ የ”ስም ፖለቲካ” ነው:: ሁሉም እናት-አባቱ ያወጡለትን ስም ጮክ ብሎ መናገር እስካልጀመረ ድረስ የግለሰብ ማንነት ከቤሄር ማንነቱ ተነጥሎ መታየት አይቻልም::

  Like

አስተያየቶቹ ተዘግተዋል፡፡