አንዳንዴ እኛ ኢትዮጲያኖች “ሞኞች” ነን!!! አለም በፍትህ የምትመራ ይመስለናል::

በHiwot Treaty እንግሊዝ ዐፄ ዩሃንስን ካደች….በWucale Treaty ኢጣሊያ ዐፄ ሚኒልክን:: League of Nations ዐፄ ሃይለስላሴን ክዶ በመርዝ ጋዝ ስናልቅ አይቶ እንዳላየ ሆነ….

ኢሳያስ እንኯ በአቅሙ መለስን አልጄስ ላይ ሲሸውደው UN ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ ዝም ብሎ እያለ አሁን #ሃይለማሪያም ደግሞ ግብፅን በ United Nations በአባይ ጉዳይ በተደራድሬ እረታለሁ ይለኛል::

ፍፁም አይሆንም!! ግብፅ ትረታናለች!! ለምን??
#አለም_በፍትህ_አትመራም!!!
ይልቅ….”አለም በፍትህ ትመራለች ይሚሉ ‘ብፁዐን’ ናቸው::”
ይህን ያለው ማን ነበር??
መለስ ዜናዊ!

በለ አሁን የመለስን ሌጋሴ ማሰፈፀም አይደል ነገሩ….
“በአባይ ግድብ ሠማይ ቤት እንጂ በምድር አልደራደርም” ብለህ ቁርጡን ተናገር::
አለበለዚያ… ይሄ ለሞላለት ብቻ የማያሽቃብጥ የይስሙላ ድርጅት, (UN) ለደሃ ሀገር ፍትህ ሰጥቶ አያውቅም!!!

እኛም ለአሜሪካ ከግብፅ በላይ አንቀርባትም!!!

Advertisements