‘አላዋቂ’ እንጂ ‘ክፉ ሰው’ የለም!!! *********************** ሃሣቡ በዘልማድ: ተግባሩ በዘፈቀደ: አመለካከቱ ባረጀ እሳቤ የተቀፈደደ:: ሳቅህ የሚሰቀጥጠው: ደስታህ የሚያስቀየመው: ስኬትህ የሚያስመቀኘው:: ይሄ ሰው: ሣቁ የዉሸት: ደስታ ያላጀበው: ሕይወቱም የከሠረ: ስኬት ያልጎበኘው:: አየህ! ለክፋት ተጠቦ: ጥቃቅን ነገሮችን አስቦ:: ቢያውቅ ኖሮ: ላያደርገው: ቢያስተውል: ላያስበው:: ይሄ ሰው: እንዲህ ሆኖ የባከነው: ክፋትን ‘ሥራ’ ያደረገው: ‘ክፉ’ ሆኖ’ አይደለም ክፋት የሚያስበው:: አላዋቂነት ነው: ቅን ልቦና የነሣው:: ከእናቱ የተማረውን: ከጡጧ ጋር አብሮ የጠባውን::

‘አላዋቂ’ እንጂ ‘ክፉ ሰው’ የለም!!!
***********************
ሃሣቡ በዘልማድ:
ተግባሩ በዘፈቀደ:
አመለካከቱ ባረጀ እሳቤ የተቀፈደደ::

ሳቅህ የሚሰቀጥጠው:
ደስታህ የሚያስቀየመው:
ስኬትህ የሚያስመቀኘው::
ይሄ ሰው:
ሣቁ የዉሸት: ደስታ ያላጀበው:
ሕይወቱም የከሠረ: ስኬት ያልጎበኘው::

አየህ!
ለክፋት ተጠቦ:
ጥቃቅን ነገሮችን አስቦ::
ቢያውቅ ኖሮ: ላያደርገው:
ቢያስተውል: ላያስበው::
ይሄ ሰው:
እንዲህ ሆኖ የባከነው:
ክፋትን ‘ሥራ’ ያደረገው:
‘ክፉ’ ሆኖ’ አይደለም ክፋት የሚያስበው::
አላዋቂነት ነው:
ቅን ልቦና የነሣው::
ከእናቱ የተማረውን:
ከጡጧ ጋር አብሮ የጠባውን::

S.T

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s