የአብዛኛው ኢትዮጲያዊ ሕይወት የሚሰማው ድምፅ የማቃት ስርቅርቅታ እንጂ የመቻል ፉከራ አይደለም!!

‘…መጀመሪያ አለማችን ተፈጠረች። ሕይወትን ያለውን ሕይወት በሌለው ጉያዋ ቀላቀለች። በዚያውም ተፈታኟን ኮለኮለች። ከእንስሳት መሀል ልብ ብሎ ሊያያት የቻለው እንስሳ እራሱን ‘ሰው” ብሎ ጠራው። እኛም ኢትዮጲያዊያን ነበርንበት።…ስልጣኔ የሚሉት ነገር እየተክተፈተፈ ተከትሏል። እኛም ኢትዮጲያዊያን ነበርንበት። ሁሉም በየአገሩ ከተፈጥሮ ጋር ግብግቡን አጧጧፈ። እኛ ኢትዮጲያዊያን ግን የነበርንበት መሆኑን እንጃ።
‘ስልጣኔን መጀመራችንን እንጂ ግብግቡ ስለመቀጠሉ መረጃው አይታይም። በአብዛኛው የሚታየው ያልተቋረጠው ድህነታችን ነው። ‘ለስልጣኔ ግብግብ ይውል የነበረው አቅማችንን ሣይሰለቅጥ መቼም ድህነታችን እንዲህ ሊደልብ አይችልም” ማለት ይቀላል። እና፣‘ድህነትእንዲህ ሊፋፋ የሚችለው ብልፅግና የሞተበት፣ ስልጣኔ የበሰበሰበት አፍር ሲያገኝ ነው’ ማለት የሚያስችል መረጃ ነው ዙሪያውን የሞላው።
‘ተከርችማ የቀረችው አጭር የሕይወት ጣሪያችን ያጨቀችው ሁሉ የሚሰማው ድምፅ የማቃት ስርቅርቅታ እንጂ የመቻል ፉከራ አይደለም። ለምን…ለምን…ለምን???
ጥያቄው ብዙ ግዜ ተጠይቆ ሊሆን ይችላል። መልስም ተሰጥቶ ሊሆን ይችላል። የተጨበጠ ልዩነት ግን የለም”
#ሚክሎል

Advertisements