ሰው የሚያምንበትን ነገር “ሲያውቀው”፣…. ናቀው – እምነቱን ነፈገው!!

ሰው የሚያምንበትን ነገር “ሲያውቀው”፣….
ናቀው – እምነቱን ነፈገው!!
*****************************
ሰው በባሕሪው የሚያምነው በማያቀው ነገር ላይ ነው። እንደ-የዘመኑ ሥልጣኔ ደረጃ የሰው ልጅ በተለያዩ ነገሮች እምነት እና አምልኮ ነበረው። የሚያምንባቸው ነገሮች ደግሞ፤ የሌሉና ከሃሣባዊ እይታ ባለፈ በዝርዝር በማያውቃቸው ነገሮች ላይ ነው። ሃሣብ ድግሞ ወደ እውነት መድረሻ መንገድ እንጂ በእራሱ ‘እውነት” አይደለም። ሰው ‘ማመን” የጀመረው እና የሚያምነው፤ ስለ መነሻ ምክኒያታቸው ግልፅ ግንዛቤ የሌለው፣ ነገር ግን፣ በሕይወት እና በእለት-ከእለት ኑሮው ላይ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩ ነገሮችና ክስተቶች እራሱን ለመጠበቅ ነው። ሰው ቀድሞ ያምንባቸው የነበሩ እንደ ፀሐይ፣ ኮኮብ፣ ጨረቃ፣… ተራራ፣ ድንጋይ፣ ሐውልት፣…ወንዝ፣ ባሕር፣ ወቂያኖስ፣… አማልክት፣ መላዕክት፣ አምላክ፣ …ወዘተ ያሉትን ነገሮች በዝርዝር ሲያውቃቸው፣ ናቃቸው። እምነቱን ነፈጋቸው…አወቃቸው! በመሰረቱ ‘ማመን” አለማወቅን ይጠይቃል። ‘አወቅኩሽ – ናቅኩሽ” ነው ነገሩ።

Advertisements