አሁን በኢትዮጲያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ይለወጣል ብለህ ከሆነ…..ወፍ የለም!!! “መሪ-የለ”…”አመፅ-የለ”…. ሁኔታው ባለበት ይቀጥላል!!!

ጉዳይህ ስለ’መብት’ ሆነ ስለ’ጥቅም’፣ ጥያቄና መልሱ ስለአንድ ነገር ነው – “ለውጥ”። በሀገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ “ጠያቂ” ሆንክ “መላሽ” ነገሩ ያው አንድ ነው – “ለውጡ አለ/የለም”። ይሄ የሚፈለገው ለውጥ “አለየመሪ/የለም” የሚለው ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው። የሚፈለገው ለውጥ የሚመጣው በሂደት ወይም በአለየመሪንድ-ግዜ ሁለገብ የሆነ ለውጥ በማድረግ ሲሆን ሁለቱም አንድ ዋና መነሻ ምክኒያት አላቸው። ለመጀመሪያው አይነት ለውጥ፣ ጠንቃቃና ብልህ፣ የችግሮችን መነሻ ምክኒያት አውቆ ወይም ገና ከመነሻቸው ለይቶ መፍትሄ መስጠት የሚችል መሪ ያስፈልጋል። ሁለተኛው ደግሞ፣ ከተለመደው የፖለቲካዊ አካሄድ ወጣ ያለ፣ አሁን ያለውን ሥረዓት በማናጋት የቆመበትን መሰረት እንዲስት በማድረግ፣ ስር-ነቀል ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ፖለቲካዊ ንቅናቄ መፍጠር ሲቻል ነው። አሁን በኢትዮጲያ ባለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ፣ የሁለቱ የለውጥ መሰረታዊ ምክኒያቶች “ፍንጭ” ጭራሽ የለም። ስለዚህ፣ አሁን ያለው ስረዓት ባለበት ሁኔታ ይቀጥላል።

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s