ኢህአዴግ ሆይ!….አንተ’ኮ “ደሞዝተኛ ሁሉ “አበል” ያለው ይመስልሃል።

ኢህአዴግ ሆይ! አንተ’ኮ “ደሞዝተኛ ሁሉ “አበል” ያለው ይመስልሃል።
.በETV ‘SHAME’ አስይዤያቸው ደሞዛቸውን ለአባይ እቆርጣለሁ ብትል…በቀጣዩ ምርጫ “MOOD” እንደምንይዝብህ እወቅ!!!
*****************************
ያኔ በጨብጥ እና ቂጢኝ ዘመን እነዱ ሴተኛ አዳሪ ጋር ሄዶ፣
“እንትን፣ በዓሣ ትለውጪያለሽ?” ይላታል።
“አዎ” ብላዉ “እንትን” አድርጎ፣ የሞተ_ዓሣ ጥግ ጣል አድርጎላት ይወጣል።

ሴተኛ አዳሪዋ ግን እንደአታለላት ወዲያው ገብቷት ኖሮ፣
“በሞተ ዓሣ አታለልከኝ? ግድየለም! አንተም #ስትሸና_ታገኘዋለህ!” አለችው።
*****************************
ለመጀመሪያ ግዜ፣ የአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል “ሙሉ የወር ደሞዛችሁን በመስጠት ቦንድ ግዙ!” ብለህ፣ ፍቃደኝነታችንን እነኳ ሳትጠይቅ ወሰድክ። በቀጣዩ አመት ደግሞ፣ ጭራሽ ሣታማክረን “መሉ ደሞዛቸውን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ለመስጠት በድጋሜ ቃል ገቡ” ብለህ በቴሌቭዥን ተናገርክ ‘ዝም” አልን።

አሁንስ እኔ መሮኛል! ለሦስተኛ ዙር ደሞዜን ጫፏን ንካና ሞክረኝ። በፍርድ ቤት አልሄድም! በ2007 ምርጫ “እፈርድብሃለው!” እንዴ! አሁንስ አልበዛም? እኔ እንደአንተ የስብሰባ አበል፣ የነዳጅ አበል፣ የቤት አበል፣ ጉዞ አበል፣ የምናምን አበል…አበል..አበል …የለኘም! እኔ የወር ደሞዜን ጠብቄ ነው የምኖረው! እሷን ዝም ብለህ መጥተህ መቁረጥ አትችልም! በቃ! እንኳን ”የአባይ ግድብ ማሠሪያ” ቀርቶ ለምን “#የገነት_በር_ማሠሪያ” አይሆንም፣ ፍቃዴ ሳትጠይቅ ደሞዜን እንዳትቆርጥ! “እሺም፣ እምቢም” ልልህ እንደምችል አስበህ… “የተከበሩ አቶ ስዩም፣ እባክዎ ደሞዝዎን ለአባይ ግድብ ማሠሪያ የስጡ”? ብለህ ጠይቀኝ። አለበለዚያ ግን፣ በETV “ለሦስተኛ ዙር ሙሉ የወር ደሞዛቸውን ቦንድ በመግዛት ለአባይ….ፕሪሪም…ፕሪሪም” እያልኩ “ለ3ኛ ግዜ ‘Shame’ አስይዛቸዋለሁ’ ብለህ ከሆነ…በቀጣዩ ምርጫ “MOOD” እንደምንይዝብህ እወቅ።