“ከአባይ ቦንድ” እና “ከሚስት-ቃል” ማን ይበልጣል?

ታክስ፣ የጡረታ መዋጮ እና “የሕዳሴ ቦንድ”፣ከአጠቃላዩ ያልተጣራ ደምዎዜ ላይ 35%ቱን ይወስዳሉ። በቀረው 65% ደግሞ፣ ከሞላ-ጎደል በሁሉም እቃና አገልግሎት ላይ የ30% VAT እከፍላለሁ። ስለዚህ፣ “እኔ የምኖረው በ35% ብቻ ነው” ማለት ነው። ምን ነው “የVAT ታክስ 15% አይደለም ወይ?” ትሉ ይሆናል። እዚህ በኪራይ ሰብሳቢነት በነቀዘች ሀገር ውስጥ፣ መንግስት እና ነጋዴ ተስማምተው ከሕብረተሠቡ 30% VAT ሰብስበው 15% -15% ’SHARE”። በፊት 3ብር ይሸጥ የነበረን እቃ፣ VAT ሲመጣ ነጋዴው ለመንግስት 15% (45 ሣነቲም) ይሰጥና፣ 55ሣንቲም ደግሞ ለእራሱ በመውሰድ፣ እና ዋጋውን 4.00 ብር አድርጎታል። “ምን ነው?” ብትለው “VAT‘ይለሃል።እስኪ “ዝም” ብላችሁ ለመታዘብ ሞክሩ? ሚስቴ ደግሞ ‘በወር 1000 ብር ቆጥብ” ብላ ሰቅዛ ይዛኛለች። ከላይ ካሉት ውስጥ ደግሞ ማስቀረት የምችለው “የሕዳሴ ቦንድ” ክፍያን ነው። ስለዚህ፣ ከዚህ በኃላ “ለሦስተኛ ግዜ ሙሉ የወር ደሞዛቸውን .ምናምን፣…ቁርጠኝነትን ማረጋገጥ” ብሎ ነገር የለም። አባይም አባይ ነው። ሚስትም ሚስት ናት። “አባይ ቦንድ” እና “ከሚስት-ቃል” ማን ይበልጣል???????