ሀበሻ_ሲመቸውም_አይቻልም! ሳይመቸውም አይቻልም! በነብይ_መኮንን

#ሀበሻ_ሲመቸውም_አይቻልም! #ሳይመቸውም_አይቻልም!
በነብይ_መኮንን
*****************
“አሁን ትምህርትህ ምን ላይ ደረሰ?”

“አሁንማ በሕክምና ዶክትሬቴን ጨርሼያለሁ?”

“ኦው! ሐኪም ነሃ! የት ትሰራለህ?”

“እዚህ ላይ ነው ጉዱ!”

“እንዴት?”

“ወዳጄ! አሜሪካን ሀገር የሕክምና ዶክትሬትህን ትይዛለህ እንጂ በቀጥታ ሐኪም ትሆናለህ ማለት አይደለም።”

“አልገባኝም። ሥራ በቀላሉ አይገኝም ወይስ አይቀጥሩህም?”

“አ..ዎ..እንደሱ ማለት ይሻላል ባክህ፣ በደፈናው።”

“ግራ አጋባኝ። እነዚህ ሀበሾች ሥራ ጋ ሲደርሱ አፋቸውን የሚይዛቸው ነገር አለ።

“ምንድን ነው ችግሩ? ማለት በተማርከው ትምህርት መስራት ክልክል ነው?”

“በጭራሽ!”

“ታዲያ አንተ ለምሣሌ አሁን ምን ትሰራለህ?

“አሁን የምሰራበት…ከአንድ ሰዓት ተኩል የመኪና ጉዞ በኃላ የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ ነው። እ..እ.. እ..ና “እዚያ ሆስፒታል ውስጥ ለግዜው የምሰራው በሽተኞች ሲመጡ ተራ ማስያዝ ነው። በቃ ማለት ማሰለፍ።”

ለትንሽ ግዜ ፀጥ አልኩ። ትንፋሽ ያጠረኝም መሰለኝ!!!
****

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s