በኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች ት/ት በምናባዊ አለም የተፃፈን_ድርሰት_እንደ_ማንበብ! ዕውቀት_የቢሆን_አለም_ዕውቀት ነው።

በኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች ት/ት
በምናባዊ_አለም_የተፃፈን_ድርሰት_እንደ_ማንበብ! ዕውቀት_የቢሆን_አለም_ዕውቀት ነው።
**************************
አሁን እንደው… በኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ፤ የምናስተምረውም ሆነ የምንማረውን ነገር ከነባራዊ እውነታው ጋር የተያያዘ ነው። በተፈጥሮ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ችግሩ የከፋ ላይሆን ይችላል፤ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ግን፣ እንኳን ከነባራዊው እውነታው ጋር ማያያዝ ቀርቶ፣ ፈረንጅ የፃፈውን ከማነብነብ ባለፈ፣ ስለነገሩ ጭብጥ እና ግንዛቤ ያለን አይመስለኝም። ለምን? አሁን የምናውቀውን የአወቅንበት መንገድ በነባራዊው እውነታ ላይ ተመስርቶ የተቀረፀ ባለመሆኑ፤ እውቀታችንም በነባራዊው እውነታ ላይ ተመስርቶ ሣይሆን፣ ልክ በሌላ ግዜና ቦታ እንደ እንደተፃፈ የልብወለድ ድርሰት አንብበን የገኘነው ስለሆነ ነው። ስንማርና ስናስተመር የምንማራቸው ፅንሰ-ሃሣቦች ልክ እንደ ድርሰት ምናባዊ አለም እንጂ የእውነታው አለም ክስተት እንደሆነ አድርገን አይደለም።ይህንንም “በቲዎሪ እንጂ በኢትዮጲያ ነባራዊ እውነታ ለመተግበር አስቸጋሪ ነው!” በማለት እናረጋግጠዋለን። ቲዎሪ (ንድፈ-ሃሣብ) ትርጉም የሚኖረው በነባራዊ እውነታ ውስጥ ሊተገበር ሲቻል እና በቅድመ-ሃሣብ ደረጃ የተቀመጠውን ውጤት መስጠት ሲችል ብቻ ነው። የአንድ ቲዎሪ ትክክለኝነት መነኪያው እኮ በነባራዊ እውነታ ውስጥ የነገሮችን መነሻ-ምክኒያት እና ውጤት በግል ማስቀመጥ ከቻለ ብቻ ነው። አለበለዚያ ከንዑስ-ሃሣብነት የዘለለ ፍየዳ የለውም። ታዲያ በኢትዮጲያ ውስጥ ባለው ነባራዊው እውነታ ውስጥ ተግባር ላይ የማይውል ከሆነ…እውቀታችን ከነባራዊ እውነታ ጋር ግንኙነት ከሌለው፣ እውቀትን ከተግባር ጋር አሰባጥረን የማህብረሰቡን ችግር መፍታት ካላስቻለን፣ “ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተማርነውን ነገር ለምን ተማርነው?” የዩኒቨርሲቲ ት/ት ማለት እኮ’ ልክ በምናባዊ አለም የተፃፈን ድርሰት እንደ ማንበብ ነው!

ቀጥሎ ባለው ሊንክ የምታገኙት የአንድ ጥናታዊ ፅሁፍ ጭብጥ-ሃሣብ “የውሸት ተማሪዎች…የውሸት አዋቂዎች” የሆነው ለምን እንደሆነ በግልፅ አስቀምጦታል።

https://ethiothinkthank.wordpress.com/2014/04/05/the-impossible-development-with-the-colonial-intellectual-roots/