ዶክተሩ..የዕቃ መጠቅለያ ወረቀት እንደሚገዛ ባለሱቅ ክብደቱን መዝኖ… “ጥሩ አልሰራህም” አለኝ።

ዶክተሩ..የዕቃ መጠቅለያ ወረቀት እንደሚገዛ ባለሱቅ ክብደቱን መዝኖ… “ጥሩ አልሰራህም” አለኝ።
የዛሬ ሣምንት “ትምህርት ሚኒስቴር በእርዳታ ፍርፋሪ ደነዝ ሕንዳዊ ቀጥሮ ትውልድ ያደነዝዛል!!!” ብያችሁ ነበር አይደል? ዛሬ ደግሞ፣ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ “ኢትዮጲያ ተጨማሪ የሕንድ መምህራንን መቅጠር ትፈልጋለች” ብለው እርፍ!!! ዘገባው ደግሞ የሚጀምረው “Ethiopia, where Indian Teachers have long been REVERED…” በሚል ዐ.ነገር ነው። እንግዲያውስ እውነቱን ልናገር…ሕንድ አገር ሄዶ MA እና Phd ሰርቶ የመጣ አንድ መምህሬ ከ20% የሚያዝ Assignment ሰጠን። “ብዙ ለፃፈ ማርክ ይሰጣል” ሲሉ ሰምቼ፣ ከኢንተርኔት በማውረድ (በእራሴ እያፈርኩ) 52 ገፅ አስረከብኩ። ዶክተሩ..የዕቃ መጠቅለያ ወረቀት እንደሚገዛ ባለሱቅ፣ የእኔን 52 ገፅ ከሌላ ተማሪ 120 ገፅ “ጥራዝ” ጋር በሁለት እጆቹ ከፍ አድርጎ ይዞ “ክብዳቸውን” ከለካ በኃላ፣ “ስዩም ጥሩ አልሰራህም” ሲለኝ ወሽመጤ ስ..ብ..ር..ነበር ያለው። በኃላ ግን ያ..ለ20 ማርክ Assignment 120 ገፅ ኮፒ ያደረገው ጓደኛዬ፣ የማስተርስ የመመረቅያ ጥናታዊ ፅሁፉ “60 ገፅ አልሞላ አለኝ” እያለ ሲጨነቅ አገኘሁት። እሱም የዩኒቨርሲቲ አስተማሪ ነው! ከዚያ በኃላ….ሕንዳዊ መምህር ወይም ሕንድ ሀገር የተማረ ኢትዮጲያዊ፣ እና ከሁለቱ በአንዱ የተማረ አስተማሪ ሳይ…”ድብተራ የሆንኩ ይመስለኛል!”
ኧረ የሰሚ ያለህ! ሕንዳዊ መምህራን ማለት እኮ ትውልድ የሚያደነዝዙ “አደንዛዥ ዕፅዎች ናቸው”

Advertisements