“በአደባባይ_እንዳልናገር_ተከለከልኩ” ካልክ “ልትናገር_የነበረው_በሙሉ_እውነት_ነው” እንደማለት….።

“#በአደባባይ_እንዳልናገር_ተከለከልኩ” ካልክ “#ልትናገር_የነበረው_በሙሉ_እውነት_ነው” እንደማለት….።
*****************************
ተቃዋሚዎች በአደባባይ ተቃዉሞ ሲያደርጉ 1) በእውነት/ዕውቀት ላይ የተመሠረተ የመቻል_ፉከራ፣ ወይም ደግሞ
2) በቢሆን_አለም_እሳቤ ላይ የተመሠረተ የማቃት_ጩኸት ነው።

1ኛው ከሆነ ለሕዝብ ሆነ ለኢሕአዴግ መልካም ነው (‘ጠልፎ በኪሴ ቢያደርጋት” ማለት ነው)። 2ኛው ከሆነ ደግሞ ያው እንደተለመደው ነው። እድሜ ቅንጅት (ውይ ሞቷል ለካ)፣ አ.አን ጨረቃ ላይ ጥሏት ከሄደ ወዲህ፣ ህዝቡ “ሆኖ” ያየውን ትቶ “ቢሆን” ብሎ የቀሰቀሰን ፓርቲ ይመርጣል ማለት ዘበት ነው።

ታዲያ ኢህአዴግ አሁን ያሉትን ተቃዋሚዎችን “የእናቴ መቀነት…” ዓይነት ምክኒያት እየጠቀሰ ተቃዋሚዎች “እሪሪሪ” እንዳይሉ የሚያደርገው ለምንድን ነው? እንደ “ህዝቡን እንዳያታልሉት…እንዳያደናግሩት”… ”ሁከትና ረብሻ እንዳይፈጠር”… ”ሃይማኖታዊ መንግስት…” ያሉ ምክኒያቶች ልክ “ህዝቡ ቅዠት እና እውነትን ለይቶ አያውቅም” እንደማለት ነው። ‘ኢህአዴግ የሚጠረጥረው ተቃዋሚዎችን ሣይሆን እራሱ “ህዝቡን” ነው’ ማለት ነው’ኮ።

ኢህአዴግ በኤሬቴድ እንደዚህ..እንዲህ ሆኖ ሲለው፣ ህዝቡ ደግሞ “መጠርጠር ነው” ይልዋል። ኢህአዴግ ሺህ ቢናገር፣ ጭውውው ካለ ደጋፊ በስተቀር፣ ለአብዛኞቻችን እውነቱ ያለው እንዳይናገሩ የተደረጉት ጋር ነው። “ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን” በሆኑበት ሀገር ሰው ከሚያየው እውነት ይለቅ የሚሰማውን “ውሸት” ይቀበላል። እኔ’ጃ…ምንልባት ጀግኖቻችን ሁሉ ሽፋታዎች፣ ፖለቲካችንም ባንዳ_እና_ሽፋታ ስለሆነ ሊሆን ይችላል። ብቻ እኔ’ጃ!