ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ….? Part-II

በከፍተኛ ት/ት ተቋማት የሚሰሩ ጥናታዊ ሥራዎች ችግር-ፈቺ፣ ተደራሽ እና ስርፀት በተጠቃሚው ዘንድ እንዳይሰርፁ በማድረግ ረገድ እጅግ በጣም ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው። አንድ ሐኪም ለሕክምና የመጣውን ግለሰብ በሚገባው ቋንቋ ህመሙን፣ ስሜቱን እና ታሪኩን ጠይቆ፣ ታካሚው የነገረውንና ያለውን የሞያ ክህሎት ተጠቅሞ መድሃኒት ያዝለታል። ሆኖም ግን፣ የመድሃኒት ማዘዣውን እና አጠቃቀሙን ታካሚው በማይረዳው ቋንቋ ፅፎ ቢሰጠው ተግባሩ የሞያውን ሥነ-ምግባር የጣሰ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ሆኖ ይወገዛል። የሐኪሙን ጤነኝነት መጠራጠር፣ አልፎ-ተርፎም “በሽተኛው ሐኪም!” በማለት ልናወግዘው እንችላለን። በመግባቢያ ቋንቋው ‘ችግርህ ምንድነው?…የቱ ነው? …ምን ተሰማህ? …ምን አሰብክ? …መፍትሄው’ስ?” ብሎ ጠይቆ፣ የተነገረውን እንደግብዓት ተጠቅሞ ጥናት ካደረገ በኋላ፣ የጥናቱን ውጤት ታዳሚው በማይግባባበት ቋንቋ ፅፎ፣ ጠርዞ በቤተ-መፅሃፍት እና በቢሮ መደርደሪያ ላይ የሚያስቀምጥ ተመራማሪ ከ”በሽተኛው ሐኪም” በምን ይለየዋል?

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s