ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ…?Part-III

“በሽተኛ ሐኪም እና ተመራማሪ” ሁለቱም አንድ ናቸው! በሚያግባባ ቋንቋ ጠይቀው በማያግባባ ቋንቋ የሚናገሩ! ነገር ግን፣ “በሽተኛው ሐኪም” ግለሰቡ ላይ ለፈፀመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ተጠያቂ ሲሆን “በሽተኛው ተመራማሪ” ማህብረሰቡ ላይ ለሚፈፅመው ተመሣሣይ ተግባር ተጠያቂ አይሆንም። የድርግት ልዩነት በመኖሩ ሣይሆን ግለሰብ የመኖሪያ አድሯሻ አለው፤ የማህብረሰብ አድራሻ ሀገር ነው። ግለሰብ እራሱን ይወከላል ወይ ይወክላል… ማህብረሰብ ይወከ’ላል እንጂ አይ’ወክልም። ግለሰብ ተሟግቶ ይረ’ታል፣ ወይ ይረታል። ማህብረሰብ ለወኪሉ አደራ ሰጥቶ ፍትህ ይጠብቃል።

የቀበሌ ሊ/መንብር ሆነ የወረዳ ኃላፊ፣ ጋዜጠኛ ሆነ የልማት አርበኛ፣ “እንግሊዘኛ በእራሱ ከመግባቢያ ‘ቋንቋነት’ አልፎ ዕውቀትና የአዋቂነት ልክ በሆነበት ሀገር፤… …እንደማይገባን …እንደማይገባው…እንደማንግባባ… ሣናውቅ ቀርቶ ነው? በእንግሊዘኛ ያዘጋጀነው ጥናታዊ ፁሁፍ የአይጥ መጫወቻ እና የሱቅ መጠቅለያ እንደሚሆን ሣናውቅ ቀርቶ ነው? ግድ-የለም! በእኛው ቋንቋ እንፃፈውና አይጧ ባታነበው፣ ባለሱቁ ያነበው ይሆናል!

Advertisements