ሐኪም በአማርኛ ጠይቆ በእንግሊዘኛ መድሃኒት ካዘዘ እራሱ ጤነኛ አይደለም! የእኛ ተመራማሪዎችስ…? Part-I

ለመሆኑ፣ ‘የጥናትና ምርምር ሥራዎች ስርፀት ለምን በሚፈለገውደረጃ ለውጥ እና መሻሻል አልመጣም?” ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ጥናታዊ ሥራዎች የጋራ መገለጫ የሆነን አንድ ነገር እንደመነሻ በመውሰድ ስለጉዳዩ ያለኝ ሃሣብ ለማብራራት እሞክራለሁ።

በማህበራዊ ሣይንስ ዘርፍ የሚሰሩ ጥናቶች በሙሉ በ’አባሪነት’ የሚያይዙት ‘የመጠይቅ ቅፅ’ አለ። ይህ ቅፅ፣ ጥናቱ በግብዓትነት የተጠቀመውን ሃሣብ፣ አስተያየት፣ መረጃ፣ አመለካከት፣…ወዘተ ለመሰብሰብ የዋለ ነው። በጥናቱ መፍትሄ ስለሚሰጠው ‘ማህብረሰባዊ ጉዳይ/ችግር’ መረጃ ለመሰብሰብ እንዲቻል የጥናቱ ተሣተፊዎች በሚናገሩት’ቋንቋ’ ይተረጎማል። ብዙውን ግዜ መጠይቅ በእንግሊዘኛ ተዘጋጅቶ ከዚያ እንደየአከባቢው፣ ወደ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግሪኛ…ወዘተ ይተረጎማል። ከመጠይቅ በስተቀር፣ የጥናቱ መረሃ-ግብር፣ ትንታኔ፣ የጥናቱ ውጤት፣ እንዲሁም በውጤቱ መሰረት የሚቀርበው የመፍትሄ/ውሳኔ ሃሣብ፤ በአጠቃላይ፣ ሁሉም የጥናቱ ሥራ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተሰርቶ ይቀርባል። ይህ በሁሉም የከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ የተለመደና ተቀባይነት ያለው አሰራር ነው።

Advertisements