በመለስ ዜናዊ ራዕይ “መንጐድ” እንጂ “መነገድ” አትችልም!!!

በ1997ዓ.ም ቴዲ አፍሮ “17 ዓመት ቁምጣ” ምንና ምን ብሎ የዘፈነ ግዜ፤ አንዳንድ ግልብ የኢህአዴግ ባለስልጣናት “ቴዲ አፈሮ ይቀርታ ይጠይቅ” የሚል ነገር አንስተው ነበር። ይሄ ነገር መለስ ዜናዊ ጋር ሲደርስ ግን፣ “እኛ ሥራችንን ብንሰራ ኖሮ፣ ይሄ ‘ዘፈን’ እንዲህ ተቀባይነት ይኖረው ነበር?” በሎ ዘፈኑም (ጃ-ያስተሰርያል)፣ እነሱም #ግልብ መሆናቸውን ያስረዳቸው። አንድ ግለሰብ በዘፈን ሆነ በፅሁፍ ሃሣቡን መግለፅ በተፈጥሮ፣ ሰው በመሆኑ ብቻ የተቸረው መብት ነው። ስልጡን ፖለቲካኛ ደግሞ፣ “ለምን እንዲህ አልክ?” ብሎ ማሣደድ ሣይሆን ‘ለምን እንዲህ አለ” ብሎ “እራሱን” ይጠይቃል። ይሄ የመለስ ዜናዊ አመለካከት ነው።መለስ ስልጡን ፖለቲከኛ ነው፣ ኢህአዴግ የሰለጠነ የፖለቲካ ድርጅት አይደልም!

ኢህአዴግ ሆይ! በአንድ በኩል “የመለስን ራዕይ እናሣካለን!” ብለህ….በሌላ ደግሞ “ጦማር ጦመርክ”…”እስላማዊ መንግስት አልክ”…”ወረቀት በተንክ”….”ሰላማዊ ሰልፍ ጠራህ”… እያልክ የምታስር ከሆነ፣ “ማንኛውም ኢትዮጲያዊ መሆን የፈለገውን ሆኖ ማየት” የሚለውን የመለስ ዜናዊ #ራዕይ “በማኮላሸት” ላይ ተጠምደሃል ማለት ነው። ስለዚህ፣ “የመለስ ዜናዊ ራዕይን “ማሳካት” የሚለው “ማኮላሸት” በሚለው ይቀየርና ‘ጉዱ’ ይዉጣ። ኢህአዴግ በመለስ ዜናዊ ራዕይ “መነገድ” አቁም!!!

Advertisements