‘ኢህአዴግ የሚጠረጥረው ተቃዋሚዎችን ሣይሆን “ህዝቡን” ነው’።

ኢህአዴግ አሁን ያሉትን ተቃዋሚዎችን “የእናቴ መቀነት…” ዓይነት ምክኒያት እየጠቀሰ ተቃዋሚዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይወጡ የሚያደርገው ለምንድን ነው? እንደ “ህዝቡን እንዳያታልሉት…እንዳያደናግሩት”… ”ሁከትና ረብሻ እንዳይፈጠር”… ”ሃይማኖታዊ መንግስት…” ያሉ ምክኒያቶች ልክ “ህዝቡ ቅዠት እና እውነትን ለይቶ አያውቅም” እንደማለት ነው። ኢህአዴግ የሚጠረጥረው ተቃዋሚዎችን ሣይሆን መላው “ህዝቡን” ነው።’ለህዝብ ጥቅም የቆመን ድርጅት ወይም ፖለቲከኛ፣ ከአጭበርባሪ ግለሰብ ወይም የግለሰቦች ስብስብ መለየት አይችልም’ እያለ ነው።

Advertisements