10_ዓመት_ሕገ_መንግስት_አክብሩ_ያለ_ለ10ዓመት_አክብር_ሲባል!!!

የእኔ እና ኢህአዴግ ስምምነታችን በመርህ ደረጃ ነው። ዋስትናችን የሆነው ሕገ-መንግስት እንኳ የመርሆች ስብስብ ነው። ከ1987 እስከ 1997ዓ.ም ድረስ የነበረው ፖለቲካ “በመርህ” ደረጃ አለመስማማት ነበር። ለ10 ኢህአዴግ “ሕገ-መንግስት አክብሩ” ይል ነበር! ። ከ1997 እስከ 2007 ዓ.ም ግን ከሞላ-ጎደል በህግና መመሪያዎች ላይ ሆነ እና ኢህአዴግ በተራው ለ10 ዓመታት “ሕገ-መንግስት አክብር” ተብሎ ቢለመን የሚሰማ አይመስልም። ህግና መመሪያዎች ሲወጡና ሲተገበሩ የተስማማንባቸውን መርሆችን የሚጥሱ ከሆነ ስምምነታችን ይፈርሣል። ያ…ኔ እኔም ሆንኩ ኢህአዴግ፣ ህግ ሆነ መመሪያ ዋስትና አይኖረንም። እንደገና አዲስ ስምምነት ሊያስፈልገን ነው ማለት ነው?????