በሚያግባባ_ቋንቋ_ጠይቀው_በማያግባባ_ቋንቋ_ለሚናገሩ_የኢትዮጲያ_ምሁራን!

በተለይ በማህበራዊ ሣይንስ ዘርፍ በሚሰሩ አብዛኞቹ ጥናታዊ ሥራዎች፣ ‘በአባሪነት’ የሚያያዘው ‘የመጠይቅ ቅፅ’….ለምን ጥናታዊ ሥራዎችን በእንግሊዘኛ እንደምናዘጋጅ ለማስረዳት ጥሩ ምሳሌ ይሆናል።

‘መጠይቅ’ በጥናቱ መፍትሄ ስለሚሰጠው ‘ማህብረሰባዊ ችግር’ መረጃ ለመሰብሰብ እንዲቻል የጥናቱ ተሣተፊዎች በሚናገሩት ’ቋንቋ’ ይተረጎማል። ብዙውን ግዜ መጠይቅ በእንግሊዘኛ ተዘጋጅቶ ወደ አከባቢው ቋንቋ ይተረጎማል። ነገር ግን፣ ከመጠይቅ በስተቀር፣ የጥናቱ መረሃ-ግብር፣ ትንታኔ፣ የጥናቱ ውጤት፣ እንዲሁም በውጤቱ መሰረት የሚቀርበው የመፍትሄ/ውሳኔ ሃሣብ፤ በአጠቃላይ፣ ሁሉም የጥናቱ ሥራ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተሰርቶ ይቀርባል።

ለምን? በአለም-አቀፍ ዕውቀት ላይ የምንጨምረው አዲስ ነገር ኖሮን ነው ወይስ ‘ለታላቋ እንግሊዝ’ የምናበረክተው ገፀ-በረከት ሆኖ ነው? እንደዚያም ከሆነ፣ እንግሊዝ በአንድ አመት የምታሳትማቸውን ጥናታዊ ሥራዎች እኛ ኢትዮጲያዊያን ‘ተመራማሪዎች’ ለመስራት 362 ዓመታት ይፈጅብናል። እ.አ.አ ከ1995 እሰከ 2006 ዓ.ም ድረስ ኢትዮጲያዊ ምሁራን ተሰርተው ለህትመት የበቁ ጥናታዊ ሥራዎች ብዛት 2,689 ነው። እኛ በ10 ዓመታት ውስጥ ያሳተምነው ሦስት ሺህ አየሞላም፣ እንግሊዛዊያን ግን በአንድ ኣመት ውስጥ፣ በ2006 ዓ.ም ብቻ 97,904፣ አሜሪካዊያን ከ100,000 በላይ ጥናታዊ ሥራዎች ሰርተው ለህትመት አብቅተዋል። ስለእኛ ሕብረተሰብ ችግር ለፈረንጆች የምንሰራበት ምክኒያት ምንድን ነው?

በሀገር ቤት ቋንቋ ጠይቆ – በባዕድ ሀገር ቋንቋ የሚመልስ አሰራር ‘ምን’ ይባላል? ሕብረተሰቡ የነገረን አጥንተን፣ አጠናቅረን፣ የደርስነበትን መደምደሚያ አብዛኛው ሕብረተሰብ በማይረዳው ቋንቋ ፅፈን፣ ጠርዘን ያቀረብነው ጥናታዊ ሥራ እንዴት’ስ ሆኖ ችግር-ፈቺ ይሆናል? በአፋርኛ፣ ሶማሊኛ፣ ሲዳሚኛ፣ ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አማርኛ፣ አገውኛ፣…ወዘተ፣ ለመጠየቅ እንጂ ውጤት እና መፍትሄውን ለመንገር የማይጠቀም አሰራር ይዘን ‘ሥራው ምን ዓይነት ስርፅት እንዲኖረው እንጠብቃለን?’

በመግባቢያ ቋንቋው ‘ችግርህ ምንድነው?…የቱ ነው? …ምን ተሰማህ? …ምን አሰብክ? …መፍትሄው’ስ?” ብሎ ጠይቆ፣ የተነገረውን እንደግብዓት ተጠቅሞ ጥናት ካደረገ በኋላ፣ የጥናቱን ውጤት ታዳሚው በማይግባባበት ቋንቋ ፅፎ፣ ጠርዞ በቤተ-መፅሃፍት እና በቢሮ መደርደሪያ ላይ የሚያስቀምጥ “ተመራማሪ” እራሱን ይመርምር! ይመርመር!

Epistemological Crisis: the concepetually colonized independent Nation!

https://ethiothinkthank.wordpress.com