መብት እና ነፃነት፡ቁ4

መብት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከማጣስ ግዴታ ጋር የተጣመረ ስለሆነ ሁለቱን በጣምራነት ማየት ያስፈልጋል። በዚህ መሰረት፣ ማንኛውም ግለሰብ በሰብዓዊነቱ ብቻ የተጎናፀፋቸውን መሰረታዊ መብቶች “ውስጣዊ የእኔና የአንተ” (internal mine and thine) በማለት በጣምራ ማስቀመጥ ይቻላል።

“ውስጣዊ-የእኔ” የግለሰቡን የፍላጎት ነፃነት ሲያመለክት፣ “ውስጣዊ-የአንተ” በሚለው ደግሞ የግለሰቡ ነፃ-ፍላጎት እንደ መብት የሚወሰደው የሌሎች ሰዎችን ነፃነት በማይፃረር መልኩ ተግባራዊ እስከተደረገ ድረስ ብቻ መሆኑን ይጠቁማል። በተመሳሳይ፣ ከተወለድን በኋላ በምናደርገው ተግባራዊ እንቅስቃሴ የሚገኝን መብት “ውጫዊ የእኔና የአንተ” (external mine and thine) በማለት ማስቀመጥ ይቻላል።

“ውጫዊ-የእኔ” አንድ ግለሰብ ባደረገው ተግባራዊ እንቅስቃሴው አማካኝነት በነገሮች ላይ ያለውን የይዞታ ባለቤትነት፤ በግል ፈቃድ እና ምርጫ የመጠቀም መብትን ያመለክታል።

“ውጫዊ-የአንተ” የሚለው ደግሞ ነገሮችን በፍቃዱ ሲጠቀም ሌሎች ሰዎች ያላቸውን የመጠቀም መብት በማይፃረር መልኩ መሆን እንዳለበት ያሳያል። ስለዚህ፣ የግለሰብን ነፃነት መገደብ አግባብ የሚሆነው የሌሎችን ነፃነት ለመከላከል ሲሆንና ሲሆን ብቻ ነው።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements
This entry was posted in Local Poitics, Philosophy, Politics, Religion on by .

About Seyoum Teshome

ነፃነት መብት አይደለም፣ ሰው መሆን ነው፣ የሕይወት ትርጉምና ፋይዳ ነው። የሰዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴ በሙሉ አንፃራዊ ነፃነትን ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ነው። ይህ ጦማር ገፅ የነፃነቴ ማሳያ፣ ሰው የመሆኔ ምልክት ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s