ያለና የሌለ

#መብት፦ የሌሎችን ነፃ ፍላጐት እና ምርጫ በማይገድብ መልኩ በነፃነት መንቀሳቀስ መቻል ነው፤

#ነፃነት፦ ያለ ምንም ውጫዊ ሃይል አስገዳጅነት #በራስ ፍላጐት እና ምርጫ መንቀሳቀስ መቻል ነው፤

#ግለሰብ፦ በራሱ የግል ስብዕና እና ምክንታዊ ግንዛቤ መሰረት ተግባራዊ እንቅስቃሴውን በራሱ ፍላጐት እና ምርጫ የሚያደርግ ፍጡር ነው፤

#ቡድን፦ የራሱ የሆነ የግል ስብዕና፣ ግንዛቤ፣ ፍላጐት፣ እና ምርጫ የሌለው ማህበራዊ ፍጡር ነው፤

#የግል ስብዕና እና ግንዛቤ የሌለው ማህበራዊ ፍጡር የራሱ የሆነ ፍላጐት እና ምርጫ የለውም፣ የፍላጐት እና ምርጫ ነፃነት የሌለው ነፃነት የለውም፣ ነፃነት የሌለው ደግሞ መብት የለውም።

#ስለዚህ “#የቡድን_መብት” ብሎ ነገር የለም።  በእውን ያለ ነገር ከሌለ ነገር ጋር ሊነፃፀር አይችልምና፣ “የቡድን መብት” ከግል መብት ጋር እኩል አይሆንም!!!

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements