ኢትዮጲያኖች ነፃነትን እንዲያገኟት ይናፍቋት…እንዲናፍቋት ይወቋት… #ethiothinkthank ላይ ሄደው ይተዋወቋት!!!

የማያውቅ ሁሉም ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ ተቋማት የተመሰረቱት የሰውን መሰረታዊ መብት፥ ነፃነትን ለማክበርና ማስከበር እንዲቻል ነው። የተለያዩ የመንግስት አካላት፤ ሕግ አውጪዎች፣ አስፈፃሚዎችና ሕግ ትርጓሚዎች፣ የሞያና ሲቭል ማህበራት፣ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ በአጠቃላይ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ስለ “ነፃነት” የጠራ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል።

ከተቋማዊ መዋቅሮች ባለፈ፣ ሕይወትን በነፃነት መምራት የሚሻ ማንኛውም ግለሰብ፣ ስለ ነፃነት አጥብቆ በመጠየቅ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ግንዛቤ ሊያዳብር ይገባል። ምክንያቱም፣ ነፃነትን ማወቅ፣ ማክበርና ማስከበር የሰለጠነ ማህብረሰብ መገለጫ፣ የዳበረ ፖለቲካዊ ሥርዓት ማሳያ ነው።

ስለ ነፃነት የጠራ ግንዛቤ በዳበረበት ማህብረሰብ ዘንድ፣ በተለያዩ አዋኞች፣ የሕግ አንቀፆች፣ ደንቦችና የአፈፃፀም መመሪያዎች…ወዘተ ፣ የሰዎች ነፃነት እንዳይጣስ የሚታገልና የሚያታግል ንቁ የፖለቲካና ሲቪል ማህብረሰብ እንዲኖር ያስችላል። የጋራ ግንዛቤ ባልዳበረበት የሕብረተሰብ ክፍል ነፃነት በተፈጥሮ የተቸረው መሆኑ ተዘንግቶ፣ እንደ ቁሳዊ ንብረት በሰዎች – ለሰዎች ይቸረቸራል።

ስለ ነፃነት የጋራ ግንዛቤ መኖር የግለሰብና የቡድን መብትን ከማክበርና ማስከበር ባለፈ የሀገርን ልዓላዊነት፣ ልማት እና እድገት ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅዖ ያደርጋል። https://ethiothinkthank.wordpress.com የተሰኘውን ጦማር ገፅ (blog address) በመጐብኘት፤ የነፃነትን ፅንሰ-ሃሳብ፣ ከህያውነትና ግዑዝነት፣ መብትና ሰብዓዊነት፣ ከሀገር ልዓላዊነትና እድገት ጋር ያለውን ቁርኝት፣ እንዲሁም ስለ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ሰፊ ትንታኔ የሚሰጡ ፅሁፎችን ማንበብ ይችላሉ።

https://ethiothinkthank.wordpress.com