ህያውነት እና ግዑዝነት

ሕይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም በእራሳቸው ተነሳሽነት መንቀሳቀስ መቻላቸው ነው። በሁሉም ሕይወት ያላቸው ነገሮች ውስጥ ያለና አንዴ ከተንቀሳቀሰ ለሁልግዜም የሚንቀሳቀስ ነገር ደግሞ “ፍላጎት” ነው። በፍላጎት ተፅዕኖ ስር ያለ ነገር፣ ፍላጎቱ በእውን እስካለ ወይም በሕይወት እስካለ ድረስ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል።

ሕይወት ባለው ነገር ውስጥ ያለ ተፈጥሯዊ “ፍላጎት” እንደ ግዜና ሁኔታው ስለሚቀያየር በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ውስጥ ይሆናል። ይህ ሕይወትን በማያቋርጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንድትሞላ ያደርጋል።

በእራስ-ተነሳሽነት የሚደረግ እንቅስቃሴ በፍላጎት መኖር ምክንያት የሚጀምር እንደመሆኑ መጠን የህያውነት እና ግዑዝነት መለያ’ ባሕሪ ነው። ስለዚህ፣ ፍላጎት ግዑዝ እና ህያው ነገሮች የሚለዩበት ተፈጥሯዊ ባሕሪ ነው። ሕይወት ያላቸው ነገሮች በፍላጎት ይመራሉ፣ በፍላጎት ይንቀሳቀሳሉ፣ በፍላጎት ይኖራሉ።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements