ተፈጥሯዊ ነፃነት እና ግዴታ

የማያቋርጥ የፍላጎት ለውጥ ለሁሉም ዓይነት አካላዊ እና ሃሳባዊ እንቅስቃሴዎች መነሻ-ምክንያት ቢሆንም፣ ተፈጥሯዊ አስገዳጅነት ያላቸው ነፃነት ካላቸው እንቅስቃሴዎች በውጤትና በባህሪ ፍፁም የተለዩ ናቸው። ሰው ተፈጥሯዊ-አስገዳጅነት ያላቸውን አካላዊ እና ሃሳባዊ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የመኖር-ህልውናውን የሚያረጋገጥ ሲሆን፣ ተፈጥሯዊ-ነፃነት ባላቸው እንቅስቃሴዎች ደግሞ “ሰብዓዊነቱን“ ያረጋግጣል።

በአጠቃላይ፣ ተፈጥሯዊ ነፃነት ያላቸው እንቅስቃሴዎች የሰው-ልጅ ከሌሎች እንስሳት የሚለይባቸው መሰረታዊ ባህሪያት ናቸው።
ለምሳሌ፣ ሰው እንደ ፅፅዋት የአካሉን ቅርፅና ይዘት እየለወጠ ያድጋል። በዚህ እና በሌሎች ተመሳሳይ የአካላዊና ስነ-ልቦናዊ ለውጦች በደመ-ነፍስ የሚመራ እንቅስቃሴ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ እንደ ማንኛውም እንስሳ፣ ሰው በስሜታዊ ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል። ሰው የሁለቱን የእንቅስቃሴዎች አጀማመር ወይም በውስጡ የሚካሄደውን የፍላጎት ለውጥ በቀጥታ ለመገንዘብ የሚያስችል ኃይል የለውም። መንስዔውን ወይም የፍላጎት ለውጥን በቀጥታ ለመገንዘብና ለመቆጣጠር ስለማይችል እነዚህን እንቅስቃሴዎች በተፈጥሮ አስገዳጅነት ያደርጋቸዋል። በአጠቃላይ፣ ሰው’ም ሆነ ሌላ አካል፣ በደመ-ነፍስ እና በስሜታዊ ግንዛቤ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ነፃነት ሊኖረው አይችልም።

ሰው እንደ ማንኛውም እንስሳ ነባራዊ እውነታን ባሉት የስሜት ሕዋሳት ይገነዘባል። ሌሎች እንስሳት የሚያደርጉት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በስሜታዊ ግንዛቤ እና በደመ-ነፍስ ነው። የሰው አዕምሮ፣ ከየትኛውም እንስሳ ጋር ሊነፃፀር የማይችል፣ እጅግ በጣም ብዙ መረጃዎችን ማጠራቀም የሚችል “ቋት” ነው። በእነዚህ አጅግ በጣም ብዙ መረጃዎች መካከል ያለውን ምክንያታዊ ተያያዥነት ለመገንዘብ የሚያስችል ከፍተኛ ተፈጥሯዊ አቅም አለው።

ለምሳሌ፣ የሰው አዕምሮ ከ24,000 የድምፅ ስሜት ማስተላለፊያዎች፣ 200,000 የሙቀት፣ 500,000 የንክኪ እና 4 ሚሊዮን የህመም ስሜት መለኪያዎች (sensors) ጋር የተያያዘ ነው። በመሆኑም፣ በእያንዳንዷ ቅፅበት እልፍ የሆነ መረጃ ወደ አዕምሮ እንደሚደርስ መገመት ይቻላል። በተመሳሳይ፣ የሰው አዕምሮ ደግሞ በሰከንድ ውስጥ 27.94 ጌጋ ባይትስ (Gb) የሚሆን መረጃን ማጠናቀር ይችላል።
በዚህ መስረት፣ የሰው አዕምሮ በስሜት ሕዋሳቱ አማካኝነት ያገኛቸውን መልዕክቶች ያጠራቅማል፣ መካከላቸው ያለውን የምክንያት-ውጤት ትስስር በመገንዘብ ወደ መረጃነት ይቀይራል። በመረጃዎቹ መካከል ያለውን ምክንያታዊ ተያያዥነት በማስተዋል በመካከላቸው ያለውን ስምምነት እና ተቃርኖ ይገነዘባል። በዚህ ሂደት ሰው ሃሳባዊ እንቅስቃሴ (thinking) ያደርጋል።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements
This entry was posted in ነፃነት, Philosophy, Politics, Religion on by .

About Seyoum Teshome

ነፃነት መብት አይደለም፣ ሰው መሆን ነው፣ የሕይወት ትርጉምና ፋይዳ ነው። የሰዎች ተግባራዊ እንቅስቃሴ በሙሉ አንፃራዊ ነፃነትን ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ነው። ይህ ጦማር ገፅ የነፃነቴ ማሳያ፣ ሰው የመሆኔ ምልክት ነው፡፡

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s