የቦታና ግዜ ገደቦች፡ቁ2

በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉት እንስሳት፣ ከዕፅዋት በተሻለ በእራስ-ተነሳሽነት ለመንቀሳቀስ የሚያስችል ተፈጥሯዊ ኃይል አላቸው። ይህ ግን እንስሳት ከዕፅዋት ፍፁም በተለየ ይንቀሳቀሳሉ ማለት አይደለም። ከዚያ ይልቅ፣ እንስሳት እንደ ዕፅዋት በደመ-ነፍስ ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ በስሜታዊ ግንዛቤ እየተመሩ ከቦታ-ቦታ መንቀሳቀስ ይችላሉ።

በመሆኑም፣ አብዛኞቹ እንስሳት በውስጣቸው ያለውን የማያቋርጥ የፍላጎት ለውጥ መገንዘብና ለዚያ ምላሽ ለመስጠት አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ስለዚህ፣ እንስሳት ከደመ-ነፍሳዊ እንቅስቃሴ በተጨማሪ በስሜታዊ ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ አካላዊ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ።

ምንም እንኳን ስለሚያደርጉት አካላዊ እንቅስቃሴ ግንዛቤ ቢኖራቸውም፣ ለእንቅስቃሴያቸው መነሻ የሆነውን የፍላጎት ለውጥ ለመገንዘብ አይችሉም። በመሆኑም፣ የሚያደርጉትን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚያስችል ተፈጥሯዊ አቅም የላቸውም።

ስለዚህ፣ እንስሳት በተፈጥሯዊ ፍላጎት አስገዳጅነት አካላዊ እንቅስቃሴ ከማድረግ ባለፈ የፍላጎት እና ምርጫ ነፃነት የላቸውም። የእንስሳት እንቅስቃሴ አማራጭና ምርጫ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ እንደመሆኑ ነፃነት ሊኖራቸው አይችልም።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s