በሦስተኛ ደረጃ ላይ ያለው ሰው ሁለት ዓይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል፤ አካላዊ እንቅስቃሴ (motion) እና “ማሰብ” (thinking)። እነዚህን ሁለት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በመገንዘብና መቆጣጠሩ ረገድ ያለው ተፈጥሯዊ ኃይል “ቀጥተኛ“ እና “ቀጥተኛ-ያልሆነ”” በሚል ለሁለት ይከፈላል።
በቀጥታ ለመገንዘብና ለመቆጣጠር በሚችላቸው እካላዊ እና ሃሳባዊ እንቅስቃሴዎች፣ የሰው-ልጅ ተፈጥሯዊ ነፃነት (freedom) አለው። በተዘዋዋሪ ወይም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ በሚገነዘባቸውና በሚቆጣጠራቸው አካላዊ እና ሃሳባዊ እንቅስቃሴዎች ተፈጥሯዊ ገዴታ፣ የተፈጥሮ-አስገዳጅነት (necessity) አለበት።