የፍላጐትና ምርጫ ነፃነት፡ቁ1

ማንኛውም እንስሳ ለተግባራዊ እንቅስቃሴው መነሻ የሆነን ተፈጥሯዊ ፍላጎት ማስቀረት አይችልም። ሕይወት የሌለው ነገር “ፍላጎት” ሊኖረው አይችልም። ከዚህ በተቃራኒ፣ በሕይወት እስካለ ድረስ “አለመፈለግ” አይችልም።

በእራሱ-ተነሳሽነት መንቀሳቀስ የሚችል ማንኛውም አካል፣ በውስጡ ለተከሰተው የፍላጎት ለውጥ ምላሽ መስጠት በሚያስችለው መልኩ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት። በመሆኑም፣ ማንኛውም ሕይወት ያለው ነገር በዚህ የማያቋርጥ የእንቅስቃሴ ሂደት ውስጥ የሚያልፍ ይሆናል።

ለምሳሌ፣ አንድ እንስሳ ያለውን የምግብ ፍላጎት ባለመፈለግ ማስቀረት፣ ወይም በሌላ ነገር ፍላጎት መቀየር አይችልም። በመሆኑም፣ ለተፈጥሯዊ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ማድረግ ካለበት አካላዊ እንቅስቃሴ እራሱን መግታት አይችልም። ይህ ለእንቅስቃሴው መነሻ የሆነውን ፍላጎት ወይም የፍላጎት ለውጥን መቆጣጠር፣ ማስቀረት ወይም መቀየር ባለመቻሉ፤ ተንቀሳቃሹ አካል የፍላጎት እና ምርጫ ነፃነት ሊኖረው አይችልም። አማራጭ እና ምርጫ በሌለበት ነፃነት የለም።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s