የፍላጐትና ምርጫ ነፃነት፡ቁ2

ሰው በስሜት ህዋሳቱ በኩል የማያቋርጥ የመረጃዎች ፍሰት እና እንቅስቃሴውን በሚቆጣጠረው የአካል-ክፍል (አዕምሮ) አማካኝነት የማያቋርጥ የመረጃዎች ቅንብር ያደርጋል። ይህ ደግሞ የማያቋርጥ የፍላጎት ለውጥ በማስከትል፣ በሕይወት ያለውን ነገር በሙሉ በማያቋርጥ የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፍ ያደርገዋል።

ለምሳሌ፣ አንድ እንስሳ ያሉት የስሜት ህዋሳት መረጃዎችን ማቀበል ቢያቆሙ፣ በውስጡ እና በአከባቢው ያለውን ለውጥ መገንዘብ አይችልም። ይህ ከሆነ በእራሱ-ተነሳሽነት ለመንቀሳቀስ አይቻለውም። ምክንያቱም፣ በስሜት ህዋሳት አማካኝነት የሚገኘው መረጃ ካልተቀናበረ እና የተከሰተውን የፍላጎት ለውጥ መገንዘብ ካልተቻለ፣ በእራስ-ተነሳሽነት እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም። ስለዚህ፣ ከሁለቱ ተግባራት አንዱ እንኳን ቢቋረጥ በሕይወት የመኖር ህልውና ያከትማል።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements