የባንዳ እና ሽፍታ ፖለቲካ

ጭፍን ደጋፊ እና ተቃዋሚ ሳይተያዩ ይጠፋፋሉ።

#ቅምሻ

“Yifat ena temuga” funny names

Pan Africa

…የይፋትና ጥሙጋ አውራጃን ጣርማበር ተራራ ላይ ሆኖ ሲመለከቱት እግዚያአብሔር ዓለምን ሠርቶ ሲያበቃ የተረፈውን ትርክምክም ያጐረበት ዕቃ ቤቱ ይመስላል። ሸለቆው፥ ጉባው፥ ተራራው፥ ገመገሙ፥ ጭጋጉ፥ አቧራው ሕይወትን አፍኗት ተኝታለች። ያቺ በሌላው አገር የምትጣደፈው፥ የምትፍለቀለቀው፥ የምትንቦለቦለው ሕይወት እዚህ እፎይ ብላለች – በርጋታ፥ በዝግታ፥ ታምማለች። በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ… ሰኞ፥ ማክሰኞ፥ ረቡዕ…ልደታ -(ራጉኤል)- አባ ጉባ – በዓታ – ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ -አቡየ ፃድቁ – የሱስ ክርስቶስ – ሥላሴ- አርባዕቱ እንስሳ – ቶማስ ሰማዕት – መስቀለ የሱስ – ቅድስት ሐና – ቅዱስ ሚካኤል – እግዚአብሔር አብ -(ሩፋኤል)- አቡነ አረጋዊ -(ገብረ ክርስቶስ)- ሕፃኑ ቂርቆስ -ኪዳነ ምሕረት -እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት – ኤዎስጣቴዎስ ፃድቅ – ገብርኤል -ህንፀታ – ማሪያም – ሐዋርያት -ጊዎርጊስ -ተክለ ሃይማኖት -መርቆሬዎስ -ዮሴፍ -መድሃኔ ዓለም -አማኑኤል -በዓለ እግዚኦ -ቅዱስ ማርቆስ -ደመራ -መስቀል -ቅዱስ ዮሐንስ -ገና -ጥምቀት -ፋሲካ – ትፈስሳለች – ትምማለች ሕይወት፥ በተገማሸረ መስክ ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውሃ—
*******
ዳኛቸው ወርቁ፥ አደፍርስ፥ ገፅ ፭ -፮

ethiothinkthank.com

View original post

ነፃነት (Liberty)፥ ክፍል-3

Pan Africa

ማንኛውም ግለሰብ አንድን ነገር በእራሱ ፈቃድ ለመፍጠር ወይም ለማድረግ የሚያስችለውን አካላዊ እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት፣ በቅድሚያ ሃሳባዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ይኖርበታል። ምክንያቱም፣ በተወሰነ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ከመሆኑ በፊት ስለ እንቅስቃሴው ማወቅ አለበት። ይህ ካልሆነ፣ በእራስ ሃሳብ ላይ ያልተመሰረተ እንቅስቃሴ በፍቃደኝነት ሳይሆን በሁኔታዎች አስገዳጅነት የሚደረግ ነው። ስለዚህ፣ በፍቃደኝነት የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ በእራስ-ሃሳብ፣ ዕውቀትና ግንዛቤ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።

ሰው፣ እውነታን ለመገንዘብና ለመረዳት፣ በዚህም በዙሪያው ስላሉ ነገሮች ምክንያታዊ ድምዳሜ ላይ ከመድረሱ በፊት፣ በቅድሚያ እራሱን ማወቅ አለበት። ስለዚህ፣ በዙሪያው ስላሉ ነገሮች ለማወቅ የእራሱን ያለበትን ነባራዊ እውነታ ማወቅ፣ የሚኖርበትን እውነታ ለማወቅ በሕይወት መኖሩን ማወቅ ይኖርበታል።

አንድ ሰው በሕይወት መኖሩን የሚያረጋግጥበት አንድና ብቸኛ መንገድ፣ በእራሱ ፈቃድ አካላዊ ወይም ሃሳባዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ነው። ሰው በፍቃዱ ለመንቀሳቀስ እንዲችል እራሱን ማወቅ አለበት፣ ለዚህ ደግሞ በእራሱ ፈቃድ መንቀሳቀስ መቻል አለበት።

ሰው አንድን ተግባር በፈቃዱ ለመከዎን በቅድሚያ ማሰብ ያለበት ሲሆን፣ ስለ ተግባሩ ለማሰብ ግን በቅድሚያ ፍቃደኛ መሆን አለበት። ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከማድረጉ በፊት፤ ምን፣ ለምን እና አንዴት እንደሚንቀሳቀስ መረዳትና ማወቅ…

View original post 19 more words

“ነፃነት” ያለ ብቻ ያሸንፋል!

Pan Africa

የእነ ዋለልኝ፣ ጥላሁን እና ማርታ ትውልድ ያነሳው የፍትህና እኩልነት ጥያቄ ለነ መለስ ዜናዊ፣ ሌንጮ ለታና ተፈራ ዋልዋ ትውልድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ መነሻ ምክንያት፣ አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት ቁልፍ የሆነ ግብዓት ነው። በወቅቱ የነበረው ፊውዳላዊ አገዛዝ ሥርዓት ከነበሩበት ዘርፈ-ብዙ ችግሮች/ክፍተቶች መካከል ለለውጥ አራማጆቹ በተለየ ሁኔታ ጐልቶ የታያቸው በፍትህና እኩልነት እጦት ምክንያት በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ላይ ይደርስ የነበረው በደልና ጭቆና ነበር።

በዚህም ፍትህና እኩልነት የሰፈነበት ሥርዓት በሀገሪቱ ለመዘርጋት የአንድ ዘመን ልጆች የተለያየ የትግል ስልት ተከትለው፣ እራሳቸውን ኢህአፓ፣ ሚኤሶን፣ ህውሃት፣ ኦነግና፣ ደርግ…ወዘተ እያሉ አደራጅተው ታገሉ፣ አታገሉ፣ ተጋደሉ፣ አጋደሉ፣ እርስ-በእርስ ተባሉ። በመጨረሻም፣ ያ ባለ ጐፈሬ ትውልድ በተየያየ ስልት ያደረገው ትግል አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ የራሱን አስተዋፅዖ አበርክቷል።

ያለፈው ትውልድ ለፖለቲካ ትግሉ እንደ መነሻ የተወሰደው የፍትህና እኩልነት ጥያቄ፣ በተለይ በትግሉ አሸንፎ ለወጣው ህውሃት/ኢህአዴግ ቅድሚያ የተሰጠውና አሁን በሀገሪቱ ለተዘረጋው ፖለቲካዊ ሥርዓት እንደ መነሻ ፅንሰ-ሃሳብ የተደርጋ የምትወሰደው የዋለልኝ (?) በብሔር እኩልነት ላይ ያተኮረች ፅሁፍ፣ ሁለቱም መሰረታዊ የነፃነት-መርህን (Universal Principle of Liberty) ማዕከል…

View original post 149 more words