“ኃይል” (Power) ምንድነው?

“ኃይል” የሚለው ቃል፡- ቻይ፣ አቅም፤ ችሎታ፣ መቻል…፤ ውጤታማነት፤ ብቃት…ወዘተ፣ ትርጓሜ አለው። በአጠቃላይ፣ ኃይል ማለት መቻል፤ አንድን ነገር ማድረግ ወይም መለወጥ መቻል። ይህን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል አቅም ያለው ነገር “ኃይል” አለው። ከዚህ በተቃራኒ፣ ኃይል የሌለው ነገር፡- የማይችል፣ አቅመ-ቢስ፣ ችሎታ-አልባ፣ ብቃት-የለሽ፣ ውድቅ፣…ወዘተ ማለት ይሆናል።

በዚህ መሰረት፣ የ“ኃይል” (Power) ፅንሰ-ሃሳብ በምክንያትነት እና ውጤትነት መካከል ባለ ግንኙነት (connection between cause and effect) ላይ የተመሰረተ ሲሆን ውጤታማነት እና ብቃትን በጋራ አጠቃሎ የያዘ ነው። ስለዚህ፣ “ኃይል” ማለት፣ አንድን ተግባር ወይም ለውጥን ለማድረግ የሚያስችል አቅም እና ብቃት ነው።

https://ethiothinkthank.wordpress.com