“ነፍስ” እና “ፍላጐት”

ፍላጎት በሁሉም ሕይወት ያላቸው ነገሮች ውስጥ ስላለና ያለ ማቋረጥ ስለሚለዋወጥ፣ ሕይወት ያለው ነገር ሁሉ፣ በሞት ወደ ግዑዝነት እስከሚለወጥበት ቅፅበት ድረስ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል። ስለዚህ፣ ሁሉም ሕይወት ያላቸው ነገሮች በዚህ ተፈጥሯዊ ፍላጎት መነሻነት ምክንያት በእራስ-ተነሳሽነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያስችል “ኃይል” (power) አላቸው። በአጠቃላይ፣ ማንኛውም ነገር ‘ተግባራዊ እንቅስቃሴ ወይም ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል ኃይል አለው’ የሚባለው፣ አንድን ተግባር የመፈፀም ወይም የመለወጥ አቅም ሲኖረው ነው።

ቀደም ባሉት ፅሁፎች ለመግለፅ እንደተሞከረው፣ ይህ ተፈጥሯዊ ፍላጐት ደግሞ “ነፍስ” ነው። ስለዚህ፣ ነፍስ ያለው ነገር ማለት በራሱ ተነሳሽነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ፍጡር ነው። በዚህ መሰረት፣ በእራሳቸው ተነሳሽነት መንቀሳቀስ የሚችሉ ነገሮች ሁሉ ይህ ተፈጥሯዊ ኃይል አላቸው። ሆኖም ግን፣ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የማድረግ ኃይል በቦታና የግዜ ተፈጥሯዊ ገደቦች የተገደበ ከመሆኑ በተጨማሪ በአካላዊ አፈጣጠር መሰረት ይለያያል።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s