ሰውን ሰው ያደረገው ማሰብ ነው

ሰው ያለውን የላቀ የማሰብ ችሎታ ምክኒያት ተግባራዊ እንቅስቃሴው ከሌሎች እንስሳት የተለየ እንዲሆን አስችሎታል። በመሰረቱ የሰው-ልጅ ከሌሎች እንስሳት አንፃር ያለው መሰረታዊ ልዩነት በዚህ ልዩ ተፈጥሯዊ ችሎታና ብቃት ምክንያት የመጣ ነው። በመሆኑም፣ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከሚያስችለው ኃይል አንፃር የሰው-ልጅ ሦስት መሰረታዊ ባህሪያት አሉት፦
አንደኛ፡- ተግባራዊ እንቅስቃሴው በአካላዊ አፈጣጠሩ የተገደበ አይደለም፣

ሁለተኛ፡- ሌሎች እንስሳት ከሚያደርጉት አካላዊ እንቅስቃሴ (physical motion) በተለየ ሃሳባዊ እንቅስቃሴ (thinking) ማድረግ ይችላል፣

ሦስተኛ፡- ከደመ-ነፍስ እና ስሜት በተጨማሪ በምክንያታዊ አስተሳሰብ እውነታን መገንዘብና መረዳት ይችላል።

እነዚህ ሰው በእራሱ-ተነሳሽነት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከሌሎች እንስሳት የተለየ እንዲሆን ያደረጉ ሦስት መሰረታዊ ባህሪያት ናቸው።

https://ethiothinkthank.wordpress.com