ስሜታዊና ምክንያታዊ ግንዛቤ

ተፈጥሯዊ ፍላጎትን በመገንዘብ ረገድ ባለው ልዩነት እንስሳት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለሁለት ክፍሎ ማየት ይቻላል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ የራሱ የሆነ ፍላጎት ያለው ማንኛውም እንስሳ በእራሱ-ተነሳሽነት መንቀሳቀስ ይችላል። ፍላጎቱን መገንዘብ የማይችል እንስሳ የራሱ የሆነ ፍላጎት ሊኖረው አይችልም። ፍላጎት ያላቸው ነገሮች በእራሳቸው ተነሳሽነት መንቀሳቀስ ይችላሉ። ለዚህ ግን በቅድሚያ ፍላጎታቸውን መገንዘብ መቻል አለባቸው።

ግንዛቤ ደግሞ በስሜት እና በምክንያታዊ አስተሳሰብ ይገኛል። ሰውን ጨምሮ ሁሉም እንስሳት ፍላጎታቸውን በስሜታቸው መገንዘብ ይችላሉ። ከሌሎች እንስሳት በተለየ፣ ሰው ተፈጥሯዊ ፍላጎቱን በስሜት እና በምክንያታዊ ስሌት መገንዘብ ይችላል።

ሰው ተፈጥሯዊ ፍላጎቱን ከመገንዘብ አንፃር ያለው ልዩነት በግንዛቤ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር አይደለም። ፍላጎትን በስሜት እና/ወይም በምክንያታዊነት የመገንዘብ ችሎታ በእንስሳቱ ተግባራዊ እቅስቃሴ ላይ መሰረታዊ ልዩነት ይፈጥራል።

ፍላጎታቸውን በስሜት በሚረዱ እንስሳት የሚያደርግ ተግባራዊ እንቅስቃሴ “አካላዊ” እና ደመ-ነፍሳዊ ነው። በዚህ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ አማራጭ እና ምርጫ የሌለውና በአካላዊ አፈጣጠር የተገደበ አድርጎታል።

ነገር ግን፣ ሰው እራሱን ጨምሮ፣ በዙሪያው ያሉ ነገሮች ዘላለማዊ በሆነና ለቅፅበት እንኳን በማያቋርጥ እንቅስቃሴ ወይም የለውጥ ሂደት ውስጥ ያሉ ቢሆኑም ይህን በቀጥታ ለመገንዘብ የሚያስችል ኃይል የለውም።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements