“ሕይወት ወይም ሞት!!!”

“ነፃነት ወይም ሞት” የሚለውን አባባል አምባገነኖች፣ አብዮተኞች፣ የነፃነት ታጋዮች…ብዙዎች ለሥርዓት ለውጥ እንደ መሪ መፈክር ተጠቅመውታል። ይህ ቁንፅል እይታ ነፃነትን በሰዎች ለሰዎች የሚቸረቸር ቁሳዊ ቅንጦት ያስመስለዋል። ነገር ግን፣ የሰው የሆነ ነገር ሁሉ ፋይዳና ትርጉሙ የሚለካው ከነፃነት አንፃር ነው። የሰው እንቅስቃሴ በሙሉ ያለውን አንፃራዊ ነፃነት ለማሳደግ የሚያደርግ ነው። ነፃነት ሰብዓዊ መብት ሣይሆን ሰብዓዊነት ራሱ ነፃነት ነው። ነፃነት በሕይወት ያለ ሰው መብት ሣይሆን ሕይወት ራሱ ነፃነት ነው። ነፃነት የሕይወት አማራጭ ሣይሆን ነፃነት ራሱ የሰው ህላዊ (ነፍስ) ነው። እና ምርጫው በነፃነት እና ሞት መካከል ሣይሆን “ሕይወት ወይም ሞት” በሚል መሆን አለበት። ነፃነቴን እንደ አማራጭ ይዞ የቀረበ አካል ነፍሴን አስይዤ ቁማር እንድጫዋት እየጋበዘኝ ነው። ይህን ቁማር ከራሱ ከሞት ጋር ካልሆነ በስተቀር ከማንም ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ አይደለሁም!!!

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements