መብት = ግዴታ= ነፃነት

…እኛ [በግለሰብ ደረጃ] የምንሻው ነፃነት ሌሎች ሰዎች ከሚሹት ነፃነት ጋር ተመሳሳይ ነው። እኛ እንዲከበርልን የምንሻው ነፃነት ሌሎች እንዲከበርላቸው ከሚሹት ነፃነት ጋር ተመሳሳይ ስለሆነ ሁሉም ሰው ከሚጠይቀው መብት እኩል የሆነ ግዴታ አለበት። የአንድ ሰው ግዴታ የመብቱ እኩሌታ እንደመሆኑ፣ መብታችን ከግዴታችን ጋር እኩል ነው። ነገር ግን፣ መብታችን ከግዴታችን ሲበልጥ የሌሎች ሰዎችን ፍላጎትና የምርጫ ነፃነት የሚጋፋ ጨቋኝ ተግባር እንፈፅማለን። ከመብታችን የሚበልጥ ግዴታ ሲኖርብን ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትና ምርጫ ተገዢ እንሆናለን። የመብትና ግዴታ እኩሌታን ያልጠበቀ እንቅስቃሴ ለጨቋኝነት ወይም ተገዢነት ይዳርጋል። ለጭቆና ወይም ተገዢነት በሚዳርግ እንቅስቃሴ ውስጥ ነፃነት ሊኖር አይችልም። በዚህ መሰረት፣ ነፃነት እንዲኖር የመብትና ግዴታን እኩሌታ በጠበቀ መልኩ መንቀሳቀስ የግድ ይሆናል። ይህ መሰረታዊ የመብት መርህ እሳቤ ሲሆን የማንኛውም ተግባር “ትክክለኝነት” ወይም “ስህተትነት” ከዚህ አንፃር የተቃኘ ነው።

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s