ተቃዋሚ_አፍቃሪ_ደጋፊ_ፍርፋሪ!!!

የሚቃወመኝ ሰው ደ…ስ ይለኛል። የእኔ ሃሳብ ትክክለኝነት በሰዎች ዘንድ ባለው ተቀባይነት የሚረጋገጥ እስከሆነ ድረስ ሃሳቤን የሚቃወም ሰው ደስ ይለኛል። እሱን ባየሁ ቁጥር ለልዩነታችን ምክኒያት በሆነው ነገር ላይ ይበልጥ እንዳስብ ያደርገኛል። የሃሳቤ ትክክለኝነት የሚረጋገጠው የሚቃወመኝን ሰው በማሳመን የሚረጋገጥ እስከሆነ ድረስ ሲቃወመኝ የእኔ እሳቤ የሕይወቱን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ እንደሆነ እየነገረኝ ነው። ምክንያቱም፣ የእኔን ሃሳብ የተቃወመው፤ ከምክኒያት፣ ግዜና ቦታ አንፃር ያለውን ነባራዊ እውነታ መሉ-በሙሉ መገንዘብ ስላልቻልኩ እንደሆነ አስባለሁ። ደጋፊዬስ…? ደጋፊዬ ከላይ የተጠቀሰውን ሃሳባዊ እንቅስቃሴ እንዳላደርግ ስለሚያግደኝ ይሰለቸኛል። የእኔን የሃሳብ ፍርፋሪ ከመቃረም በቀር ለሃሳባዊ እንቅስቃሴ ግብዓት የሚሆን ነገር የለውም።  “በምለው ነገር ሁሉ ከሚስማማ ሰው ምንም ነገር ተምሬ አላውቅም” ያለው ማን ነበር?

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements