አፍቃሪ

ይሄ ችኩል ልቤ ሁሌም ይሳሳታል
የመጣውን ሁሉ ስቆ ይቀበላል
የሄደውን ሁሉ አልቅሶ ይሸኛል

ይሄ ገራም ልቤ፣ ሲነግሩት አይሰማም
ያሉትን አመነ፣ ሊያፈቅር ነው ዛሬ’ም

ይህን ሞኝ ልቤን፣ ንገሩኝ ምን ላርገው
መጥላት አይችልበት፣ ማፍቀር አይሰለቸው
-*****-
ስዩም.ተ

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements