እሳትና አበባ

እሷ ቀበጥ፣ ቅብጥብጥ
ለግላጋ ውብ ሰንበሌጥ
ፀባይና አመሏ የማይጨበጥ።
ሲያሻት አበባ፣ የፅጌረዳ እንቡጥ
ሲነሳባት እሳት፣ የሣት ረመጥ። ስትደሰት፣ ደስታዋን የምደብቅ
ስትከፋ፣ ለሰው ብላ የምትስቅ
አወዛጋቢ፣ ስሜቷ የማይታወቅ።
እንዳያቅፏት እሳት፣ ነፍስ የምትልጥ
እንዳይገፏት አበባ፣ ተሰባሪ ቀንበጥ።
ኤጭ! ይሄ ነው’ዴ ፍቅር?
በፍርሃት ሲዋዥቁ መኖር።
*****
ስዩም ተ.

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements