እንኳንም ኢትዮጲያዊ ሆንኩ!!

ያለምንም አዕምሯዊ ብስለት ከግመል እረኝነት ወደ ሃብታምነት ሲቀየር የንፁሃንን አንገት በመቅላት የሞራል-የበላይነትን ለማግኘት የሚጥር ህሊና-ቢስ አውሬነቱን በራሱ መሰከረ፤ የአል-ነጋሺ ልጆችን እስላም ‘አይደላችሁም’ ብሎ በካራ ሲቀላ ራሱን የሰውነት ክብር አሳጣ፣ በውስጡ ያለውን የበሰበሰ የሞራል ስብዕና አጋለጠ።
በባርነት የላሸቀ ማንነቱ፣ በቅድመ-አያቱ መሬት ላይ በሃይል የሰፈረን ነጭ እንዳያይ ጋርዶት፣ አምልኮት እየሰገደለት፣ ከማንም በፊት የሰውነት ክብር የሰጠውን፣ ለመብቱ የተከራከረለትን ኢትዮጲያዊ በጠላትነት የፈረጀ ደቡብ አፍሪካዊ ድንቁርናውን በራሱ መሰከረ፣ ሰውን በጐማ አቀጣጥሎ ሲያነድ ከሰውነት ክብር ራሱን አውርዶ ህሊና-ቢስ ግዑዝ ፍጥረት መሆኑን አረጋገጠ።

እርግጥ ነው ደሃዎች ነን፣ ግን ድህነት የሞራል ስብዕናችንን አልቀማንም። እኛ ኢትዮጲያኖች’ኮ የችጋር ጣዕረ-ሞት በመጣብን ግዜ እንኳን የዛፍ ቅጠል በላን እንጂ የሰው ስጋ አልበላንም። እነዚህ’ኮ በሰው-ልጅ ደም ፌሽታ የሚራጩ አውሬዎች ናቸው! ሰው በእሳት ነዶ ሲከስል  የሚስቁ ኢ-ሰብዓዊ ፍጡራን ናቸው!

ታዲያ ይሄ ሁሉ ዘግናኝ ድርጊት በእኛ በኢትዮጲያዊያን ላይ ከእልህና ቁጭት በቀር የሞራል-ኪሣራ አያመጣምም፣ አላመጣም! ስብዕናችንን አያሳጣንም! የሞራል የበላይነታችንን አይቀማንም!

እኔ ኢ.ት.ዮ.ጲ ያ.ዊ ነኝ! በሰው ደስታ የምደሰት፣ በሰው ስቃይ የምሰቃይ ሰብዓዊ ፍጡር ነኝ። በባርነት እንደደነቆረ ደቡብ አፍሪካዊ፣ ወይም በባዶነት እንደአበደ አረብ፣ በሰው ስቃይ የምደሰት፣ በሰው ደስታ የምሰቃይ እርኩስ ፍጥረት አይደለሁም! እንኳንም ኢትዮጲያዊ ሆንኩ!!!

https://ethiothinkthank.wordpress.com