የተሳሳተ ፍቅር

ፍቅሬ ‘ስህተት ነው’ ስትይኝ
እንዲሰማሽ የተሰማኝ
ምንው አንዴ ባፈቀርሽኝ?
እንዲሰማሽ ህመሜ፣
እንዴት ቅስም እንደሚሰብር
እኔም “ስህተት ነው” እልሽ ነበር
ግን፣ ምንም ቢሆን ምንም
ሰው ፈልጐ አያፈቅርም

እና…
ልክ በፍለጋ እንደሚገኝ
“ፍቅርን ፈልግ” ስትይኝ
በጣም ነበር የገረመኝ
እስኪ አንቺ ከቻልሽ
አንድ ነገር ላስቸግርሽ
ልለምንሽ፣ ውለታ ዋይልኝ
ፍቅሬን በጥላቻ ቀይሪልኝ?
ባክሽ እስኪ ተለመኚኝ
ዘልፈሽ አስቀይሚኝ
ክብረ-ቢስ አድርጊኝ
እሳት ሁኚ፣ እሳት
ነፍሴን እስኪጨንቃት
አንድጃት፣ አቃጥያት…
መኖር እስኪያስጠላኝ
እንዲያ ለስቃይ ዳርገሽኝ
በፈገግታሽ ካልዳንኩኝ?
ያኔ ከምር ጠልቼሻለሁኝ
*****
ስዩም ተ.

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements