ብሔር እና ቋንቋ

“…የየጐሳ ልጆች ያስመሰለን ታሪካዊ አጋጣሚና በቦታ መወሰን ምክንያት ግማሾቻችን የአንዱን ነገድ ቋንቋ፣ ሌሎቻችን ደግሞ የሌላውን ነገድ ቋንቋ ስለምንናገር ነው። ለምሳሌ፥ ደምቢያን (ጎንደርን) እና ጎጃምን የወሰዱ ኦሮሞዎች የልጆቻቸው ቋንቋ አማርኛ ሆኗል፤ አማራ መስለዋል። የአርሲ ሕዝብ ከግማሽ በላይ የሐድያ ትውልድ ሆኖ ሳለ ቋንቋው ኦሮምኛ ሆኗል፤ ኦሮሞ መስሏል።…የምንናገረው ቋንቋን ተከትለን ኢትዮጲያ ውስጥ የተፈፀሙትን ድርጊቶች ያንዱ ወይም የሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ታሪክ እናድርግ ብንል እውነት አትፈቅድልንም። የአያቶቻችን ልጆች መሆናችንን በማያጠራጥር ግምት የምንደርስበትን ያህል የቅድመአያቶቻችን ቋንቋ ምን እንደነበረ አንደርስበትም…”
የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፥ ገፅ 167

የጎንደርን መሳፍንት አገዛዝ የጀመሩት ትልቁ ራስ አሊ ልጃቸው ወይዘሮ ከፈይ፣ መርሳ በሬንቱን አግብተው ጉግሣ ይወልዳሉ። ራስ ጉግሣ ይማም፣ ማርዬ፣ ዶሪ፣ እና አሉላን የተባሉ ልጆችን ወለዱ። ራስ አሉላ እትጌ መነንን (በትክክለኛ ስሟ “ፋጡማ“ን አግብተው ራስ ትንሹ ራሽ አሊን ወለዱ። የአጎታቸውን የራስ ዶሪን ሞት ተከትሎ በ1822 ዓ.ም በ12 ዓመታቸው ነገሱ)። የራስ አሊ የትውልድ አገራቸው የጁ ነው። ሁሉም የየጁ ኦሮሞች ናቸው። 

…የጎንደርን መሳፍንት አገዛዝ የጀመሩት ትልቁ ራስ አሊ ልጃቸው ወይዘሮ ከፈይ፣ መርሳ በሬንቱን አግብተው ጉግሣ ይወልዳሉ። …በ28 ዓመት የምስፍንና የግዛት ዘመናቸው ሶስት ንጉሶችን አለዋውጠዋል፤ ያለዋወጧቸውም አፄ ጊጋር፣ አፄ ኢዮአስ፣ አፄ ጓሉ ናቸው።ራስ ጉግሣ አራት ልጆች ነበሯቸው፤። እነሱም ይማም፣ ማርዬ፣ ዶሪ፣ አሉላ ይባላሉ። ራስ ጉግሣ ከሞቱ በኋላ ልጃቸው ይማም፣ ይማም ሲሞት ወንድማቸው ማርዬ፣ ማርዬ ሶስት ዓመት ገዝቶ ሲሞቱ ወንድማቸው ራስ ዶሪ ወረሱ፣ እሳቸውም ለሶስት ወር ከገዙ በኋላ የራስ ጉግሣ የልጅ ልጅ የሆኑት የራስ አሉላ ልጅ አሊ ራስ ተብለው በ1822 ዓ.ም ዓ.ም የምስፍንናውን ቦታ ሲይዙ ምፅርሐ አምባ በእሥር ከተቀመጡት የነገሥታት ልጆች መሀል ገብረ ክርስቶስን አስመጥተው አፄ ግብረ ክርስቶስ አሰኝተው አንግሰው እሳቸው ሥልጣኑን ያዙ።”

ጳውሎስ ኞኞ (1985)፣ አጤ ቴዎድሮስ፣ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት፣ የመጀመሪያው እትም በግንቦት ወር 1985 ዓ.ም ታተመ፣ ገፅ 34- 42

https://ethiothinkthank.wordpress.com