ከድንቁርና ግርዶሽ ገለጥ አድርጐ ያየ፤ አክሱም-ፅዮን በአክሱም ስልጣኔ ብስባሽ ላይ የበቀለች አረም መሆኗን ይረዳል።

ስልጣኔ የሚሞተው፣ ብልፅግና የሚበሰብሰው፣ ልማት እና እድገት የሚጠፋው የሥልጣኔ አቅም፣ የለውጥና መሻሻል መንፋስ ከሕብረተሰቡ ውስጥ በሂደት ሲሸረሸርና ሲጠፋ ነው። ይህም የሚሆነው በተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መካከል ያለው “ልዩነት” ሲጠፋ፤ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍሎች በተመሣሣይ በሆነ እምነት፣ መርህ እና መመሪያ ሲመሩ ነው።

በቻይና፣ በአክሱም፣ በግብፅ፣ በሕንድ፣…ወዘተ፣ የሥልጣኔ ማዕከል በሆኑ ቦታዎች ሁሉ፣ ሃይማኖት የሥልጣኔ መሰረት የሆነውን “ልዩነት”ን በ”ተመሣሣይነት” እየተካ፣ በሕብረተሰቡ የተለያዩ ክፍሎች ዘንድ የነበረውን “የእድገት እና መሻሻል መንፈስ” (the spirit of progress and imporvement) እየሸረሸረ ሲያጠፋው ነው። ሃይማኖት የሥልጣኔ ቅልጥም ሰብሮ ቅስሙን ልሶ፣ አጥንቱ ግጦ የሚበላ አደንዛዥ የሆነ ስርዓት፣ የአስተሳሰብ ባርነት፣ የጨቋኝ ድንቁርና መንስዔ ነው።

https://ethiothinkthank.wordpress.com