“በእውነት!”

አዎ…አውቃለሁ
“በእውነት አፈቅርሻለሁ!”
እያልኩ ዋሽቼያለሁ
እንዲያ፣ በውሸት እየማልኩ
በፍቅር እንዳልቀለድኩ
ይሄው፣ አሁን “እውነት!” ስል
ዋሾነቴን ይመሰክራል፣
ሃቄን ይመዘብራል።
-******-
ስዩም ተ.

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements