የመኖር ዕዳ

ለምድነው የምኖረው፣
መኖሬ ፋይዳ አለው
ወይስ ሞት’ን ፈርቼ ነው?

የመኖርን ፋይዳ ሣላውቅ
ትርጉሙን ሳልጠይቅ
የምኖረው ሕይወት
መጨረሻው ከሆነ ሞት
ሞትኩ’ም፣ ኖርኩ’ም ያ…ው ናቸው
አንዱን ከሌላው ምን ለየው።
ያ… ከሆነ ደግሞ
አንዱን ከሌላው አስቀድሞ
እንዴትና ለምንድነው፣
ከሞት መኖር የሚሻለው?

የምኖርለት ነገር አለኝ?
አላውቅም፣ ካወቃችሁ አስረዱኝ።
ከሞትኩ ግን የለሁም
የነፍስ ዕዳ የለብኝም።
የምኖርለት ነገር ሳይኖረኝ፣
ለመኖር ብቻ ከኖርኩኝ
ከሞተ ሰው ምን ለየኝ?
ፋይዳ የሌለው ሕይወት
ጭለማ ነው እንደ ሞት
ህልውና የሌለበት፣
ራስን የማያዩበት።

እ…ኮ ለምንድነው የምኖረው?
የመኖሬ’ስ ፋይዳ ምንድነው።
የሕይወትን ትርጉም አስረዱኝ
አሊያም ተውኝ፣ አትቀስቅሱኝ።
ተው…ኝ በቃ ‘ዝ…ም’ በሉኝ
መኖሬን አታስታውሱኝ!!
-*****-
ስዩም ተ.

https://ethiothinkthank.wordpress.com

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Please log in using one of these methods to post your comment:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s