ነፃነት የሌለው እድገት፡ አምባገነንነት

መንገግስት ኢኮኖሚው እያደገ ነው በሚለው ፍጥነት በዘርፉ ላይ ያለውን ቁጥጥር እየቀነሰ ካልሄዴ Developmental State ብሎ ነገር የለም። ደ.ኮሪያዎች ፋብሪካን በግድ “ይህን ያህል አምርት” እስከማለት ድረስ  በኢኮኖሚያዊው እንቅስቃሴ ጣልቃ-ይገቡ የነበረ ቢሆንም በእድገቱ ፍጥነት ልክ ቁጥጥሩን እየቀነሱ በመሄዳቸው ውጤቱ፡ እድገት + ነፃነት = ልማት ሆነ።
እኛስ? ኢኮኖሚው እንደፈጣን ባቡር ተምዘገዘገ እያልን በሁሉም ዘርፍ ቁጥጥሩን እናጠብቃለን። አዲስ ነገር ብርቃችን፣ ለውጥ ጠላታችን ነው። ኢኮኖሚው በደርግ ዘምን ከነበረው በስንት እጥፍ አድጓል እያልን ለስንትና ስንት እጥፍ ህዝብ ስኳር፣ ዘይት፣ዱቄት እንቸረችራለን። አንዱን እንመርጥ እንደሁ እንጂ በDevelopmental State እሳቤ መሰረት እድገት እና ችርቻሮ አብረው አይሄዱም።

እስኪ ያሳያችሁ፣ ሌላው አለም ለግማሽ ክ.ዘመን የተጠቀመው ATM ለእኛ ውስብስብ ቴክኖሎጂ ሆኖ አዲስ ለማውጣት 3 ወር ፈጅብኝ፣ አሁን ደግሞ ተሰብሮብኝ ለማስቀየር ብሄድ ሌላ 3 ወር እንደሚፈጅ አረዱኝ። የሞባይል ሲም አሁን እንዲህ በነፃ ተለምኖ ሊታደል የከፈልኩት 368 ብር ትዝ ሲለኝ ግዜ “Hey….you damn Manager, ATM & SIM are the same! Have you noticed that mr. Papous” ልል ነበር፣ እ…ተውኩት። ወደ ውጪ ከወጣሁ በኋላ ዞሬ የባንኩን ስም ደግሜ ደጋግሜ ማንበብ ጀምርኩ፦ #የኢትዮጲያ_ግድ_ባንክ ይላል። 
ለማንኛውም ይህን እንዳስብ ያደረገኝ ይህን የሮይተርስ ዘገባ ጋበዝኳችሁ።
http://in.mobile.reuters.com/articleidINKBN0LC0DB20150208?irpc=932

ethiothinkthank.com

Advertisements